የሩሲያ የቅርብ ጊዜ የጦር መሳሪያዎች እና የአዲስ ጦር መሳሪያዎች እውነታ - ክፍል 1
የሩሲያ የቅርብ ጊዜ የጦር መሳሪያዎች እና የአዲስ ጦር መሳሪያዎች እውነታ - ክፍል 1
ሩሲያ እየጨመረ የመጣውን የጂኦፖሊቲካዊ ውጥረት ለመቋቋም በተዘጋጁ አራት አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች ስርዓቶች የኒውክሌር ትሪያድዋን አጠናክራለች።
ስፑትኒክ የእያንዳንዱን መሳሪያ ልማት በዝርዝር በተለያዩ ልጥፎች ይሸፍናል።
ቡሬቬስትኒክ፦ የሩሲያ ዓለም አቀፍ ክልል የኒውክሌር ኃይል ክሩዝ ሚሳኤል
ዓላማ፡- የአየር እና የሚሳኤል መከላከያ ስርዓቶችን ማለፍ እንዲችል ተደርጎ የተነደፈ አህጉር አቀፍ የኒውክሌር ኃይል ክሩዝ ሚሳኤል።
ቁልፍ ሙከራ፡- ጥቅምት 11፣ 2018 ዓ.ም በተሳካ ሁኔታ የተሞከረው የሩሲያ ሚሳኤል በ15 ሰዓታት ውስጥ 14,000 ኪ.ሜ ሸፍኗል።
የአሠራሩ የጊዜ ቅደም ተከተል፦
◾ፅንሰ-ሀሳቡ የተጀመረው አሜሪካ ከፀረ-ባሊስቲክ ሚሳኤል ስምምነት መውጣቷን ተከትሎ በታህሳስ ወር 1994 ዓ.ም ነው።
◾በ2001 በፕሬዝዳንት ፑቲን ይፋ ቢደርግም የመጀመሪያው ስኬታማ ሙከራ በ2009 ተከናውኗል።
የሙከራ ቦታ፦ ሙከራው በኖቫያ ዜምሊያ ደሴቶች ላይ እንደተካሄደ የኖርዌይ የስለላ ድርጅት አረጋግጧል።
የስምሪት ዕቅዶች፦ ፑቲን ቡሬቬስትኒክን ከሩሲያ ጦር ጋር ለማዋሃድ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፤ ነገር ግን ከውጊያ ዝግጁነት በፊት ተጨማሪ ሥራ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡
የቡሬቬስትኒክ ልዩ ባህሪያት፡
የኒውክሌር ሞተር፡- ያልተገደበ ክልል እና ረዥም የበረራ አቅም ይሰጣል።
የክትትል አቅም፡- ለረጅም ጊዜ ሊሠራ ይችላል፣ የዋልታ መስመሮችን ጨምሮ አቅጣጫውን ባልተጠበቀ ሁኔታ በመለወጥ ከልየታ የማምለጥ ብቃት አለው፡፡
ስውርነት፡- ዝቅ ብሎ መብረሩ፣ አቅጣጫ መለዋወጡ እና ለረዥም ጊዜ የማንዣበብ አቅሙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን በማወሳሰብ ለመከታተል አስቸጋሪ ያደርገዋል።
ቴክኒካዊ ዝርዝሮች፦
▪ሞተር፡ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ።
▪የጦር ጭንቃልት፡ ኒውክሌር።
▪ክልል፡ ያልተገደበ።
▪ፍጥነት፡ ሰብሶኒክ ወይም ሱፐርሶኒክ (850-1,300 ኪ.ሜ/በሰዓት)።
▪የበረራ መገለጫ፡ ዝቅተኛ ከፍታ (25-100 ሜትር)።
▪አቅም፡- ፑቲን እና ጌራሲሞቭ አፅንዖት እንደሰጡት "በጥብቅ በሚጠበቁ ኢላማዎች ላይ የተረጋገጡ ትክክለኛ ጥቃቶች"።
የድርብ አጠቃቀም ቴክኖሎጂዎች፦
የሲቪል አቅም፡- ቡሬቬስትኒክ እና ሌሎች የላቁ ስርዓቶች የአርክቲክ ልማት እና የጠፈር አሰሳን ጨምሮ የሲቪል ዘርፎችን ሊጠቅሙ ይችላሉ።
◾ፑቲን በአነስተኛ ደረጃ የኒውክሌር ኃይል፣ በአርክቲክ የኃይል ማመንጫዎች እና በጨረቃ ተልዕኮዎች ውስጥ አተገባበሮችን ጠቁመዋል።
ይህ ሚሳኤል ለመከላከያም ሆነ ለሲቪል ኢንዱስትሪዎች ሰፊ አንደምታ ያለው እያደገ የመጣው የሩሲያ ጦር መሳሪያ አቅም ወሳኝ አካል ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X