ዳንጎቴ ግሩፕ በዚምባብዌ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ሊያደርግ ነው
11:52 13.11.2025 (የተሻሻለ: 11:54 13.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዳንጎቴ ግሩፕ በዚምባብዌ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስት ሊያደርግ ነው
ባለፀጋው አሊኮ ዳንጎቴ ለሲሚንቶ እና ለኃይል ማመንጫዎች ግንባታ ስምምነት ተፈራርመዋል። ኢንቨስትመንቱ የነዳጅ ቧንቧ፣ የሲሚንቶ ኢንዱስትሪ ተቋማት፣ የኢነርጂ ዘርፍ መሠረተ ልማት፣ የዘይት ቧንቧዎች፣ የነዳጅ ማጣሪያ እና የማዳበሪያ ምርትን ያቅፋል።
በአስር ሀገራት የሲሚንቶ ንግዶችን የሚያስተዳድረው ዳንጎቴ፤ በዚምባብዌ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው የገለጸው በ2015 ነበር። በወቅቱ በዓመት 1.5 ሚሊዮን ቶን የማቀነባበር አቅም ያለው የ400 ሚሊዮን ዶላር ሲሚንቶ ፋብሪካ መገንባት የእቅዱ አካል ነበር።
ይሁን እንጂ ይህን ፕሮጀክት ጨምሮ ለውይይት ባቀረቧቸው ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ከቀድሞው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ጋር መስማማት አልተቻለም።
ዳንጎቴ የወቅቱ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ በማድረግ፣ ግልጽነትን በማረጋገጥ እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በተሳካ ሁኔታ በማነቃቃት ላደረጉት ጥረት ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።
“ኢንቨስት ለማድረግ አሁን ትክክለኛው ጊዜ እንደሆነ እምነት አሳድሮብናል” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X