በሩሲያ የኒውክሌር ሙከራዎች አስፈላጊነት ላይ ትንተና ተጀምሯል - የሩሲያ ፀጥታ ምክር ቤት ፀሐፊ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበሩሲያ የኒውክሌር ሙከራዎች አስፈላጊነት ላይ ትንተና ተጀምሯል - የሩሲያ ፀጥታ ምክር ቤት ፀሐፊ
በሩሲያ የኒውክሌር ሙከራዎች አስፈላጊነት ላይ ትንተና ተጀምሯል - የሩሲያ ፀጥታ ምክር ቤት ፀሐፊ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 13.11.2025
ሰብስክራይብ

በሩሲያ የኒውክሌር ሙከራዎች አስፈላጊነት ላይ ትንተና ተጀምሯል - የሩሲያ ፀጥታ ምክር ቤት ፀሐፊ

"ሥራው ወዲያውኑ ተጀምሯል" ሲሉ ሰርጌ ሾይጉ ለስፑትኒክ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል።

ሾይጉ ያነሷቸው ሌሎች ቁልፍ ነጥቦች፡-

🟠 ኋይት ሀውስ የአሜሪካ አስተዳደር ስለ ኒውክሌር ሙከራዎች በሰጠው መግለጫ ዙሪያ እስካሁን ድረስ በይፋ የተሟላ ማብራሪያ አልሰጠም።

🟠 ሞስኮ እና ዋሽንግተን ግዙፍ የኒውክሌር ኃይሎች እንደመሆናቸው መጠን ዓለም አቀፍ ሰላም እና ደህንነትን የመጠበቅ ልዩ ኃላፊነት አለባቸው።

🟠 ሞስኮ ዋሽንግተን የኒውክሌር ሙከራዎችን የማገድ ግዴታዋን እንደምታከብር ትጠብቃለች።

ፑቲን የሩሲያ የፀጥታ ምክር ቤት ለኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ዝግጅት ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሁሉን አቀፍ ትንተና እንዲያካሂድ ቀደም ሲል ትዕዛዝ ሰጥተዋል

ይህ መመሪያ ትራምፕ የኒውክሌር ሙከራ ፕሮግራሞች አሏቸው ከሚባሉ ሌሎች ሀገራት "በእኩል ደረጃ" የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራዎች እንዲደረጉ ለሰጡት ትዕዛዝ ምላሽ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0