የአሜሪካ መንግሥት በታሪክ ከረዥሙ መዘጋት በኋላ መከፈቱ ይፋ ሆነ

ሰብስክራይብ

የአሜሪካ መንግሥት በታሪክ ከረዥሙ መዘጋት በኋላ መከፈቱ ይፋ ሆነ

ትራምፕ ኮንግረስ ባፀደቀው ጊዜያዊ በጀት ላይ ፊርማቸወን በማኖር የመንግሥት የ43 ቀናት መዘጋት አብቅቷል፡፡ ሰነዱ የገንዘብ ድጋፍ እስከ ታህሳስ 23 እንዲራዘም አስችሏል፡፡

ከመስከረም 21 ጀምሮ የግዳጅ እረፍት ላይ የነበሩ የፌደራል ሠራተኞች ዛሬ ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰዋል። ሴኔት እና ኮንግረስ መስተጓጎልን ለማስቀረት ስምምነት ላይ የደረሱ ቢሆንም በሙሉ ዓመታዊ በጀት ላይ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ መስማማት ካልቻሉ የመንግሥት መዘጋት ዳግም ሊከሰት ይችላል።

ኋይት ሀውስ፤ መዘጋቱ የ4ተኛው ሩብ ዓመት እድገት በ2 በመቶ እንዲቀንስ ማድረጉን አሳስቧል። ትራምፕ በመጀመሪያ የሥልጣን ዘመናቸው ያጋጠመውን የ35 ቀናት የመንግሥት መዘጋት በማለፍ በበርካት ቀናት የመንግሥት መዘጋት ሌሎች የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶችን በልጠው ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0