በሰሜን ናይጄሪያ የክርስቲያኖች የዘር ማጥፋት እየተካሄደ አይደለም - የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር
10:40 13.11.2025 (የተሻሻለ: 10:44 13.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሰሜን ናይጄሪያ የክርስቲያኖች የዘር ማጥፋት እየተካሄደ አይደለም - የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር
"በሰሜን ናይጄሪያ እየሆነ ያለው ነገር በሱዳን ወይም በምስራቃዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ከምናያቸው አይነት ጭካኔዎች ጋር ምንም ተመሳሳይነት እንደሌለው ግልጽ የሚያደርግ መግለጫ አውጥተናል" ሲሉ መሀሙድ አሊ ዩሱፍ ተናግረዋል፡፡
የቦኮ ሀራም* የመጀመሪያ ተጠቂዎች ከክርስቲያኖች ይልቅ ሙስሊሞች መሆናቸው በሰነድ የተደገፉ መረጃዎች እንደሚያሳዩ በተባበሩት መንግሥታት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ሁኔታውን "ዘር ማጥፋት" የሚል ፍረጃ የሚሰጡ መግለጫዎች ውስብስብ ሁኔታን በማቃለል፤ ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል ሊያደርግ ይችላል ብለዋል፡፡
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በናይጄሪያ የክርስትያኖች የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል በሚል የእስልምና ታጣቂዎችን ለመዋጋት ወታደሮቻቸው እንዲዘጋጁ ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል። ሆኖም ናይጄሪያ የፀረ-ሽብርተኝነት ጥረቷን በማጉላት ክሱን ውድቅ አድርጋለች፡፡
* ቦኮ ሃራም በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ ሀገራት በሽብርተኝነት የተፈረጀ ቡድን ነው፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X