ለሴቶች የመሬት ባለቤትነት እንቅፋት የሆኑ የባሕል አድሎዎችን መታገል ይገባል - ጋናዊ አጥኚ

ሰብስክራይብ

ለሴቶች የመሬት ባለቤትነት እንቅፋት የሆኑ የባሕል አድሎዎችን መታገል ይገባል - ጋናዊ አጥኚ

ጋና ውስጥ የሚያርሱትን መሬት በባለቤትነት የያዙ ሴቶች ቁጥር ከ20 በመቶ እንደማይበልጥ በጥናታቸው ማረጋገጣቸውን፤ በጋና ዩኒቨርሲቲ የሌጎን ዓለም አቀፍ ጉዳዮች እና ዲፕሎማሲ ማዕከል አባል የሆኑት ሪችመንድ አዳምቴ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል፡፡

"50 በመቶ የሚሆነው የጋናውያን ግብርና የሚከወነው በሴቶች መሆኑን ስታሰብ አድሎው ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ ትረዳለህ፡፡ ባሕሉ ለይዞታ ባለቤትነት ቅድሚያ ለወንዶች ስለሚሰጥ ሴቶች በብድር አሊያም በቤተሰብ ባለቤትነት ሥር በሚገኙ መሬቶች ላይ ጥገኛ ለመሆን ይገደዳሉ" ብለዋል፡፡

ባለሙያው ጥናታቸውን መሠረት በማድረግ የሴቶችን የመሬት ባለቤትነት የሚያረጋግጡ አስገዳጅ ሕጎች ሊኖሩ እንደሚገባም ምክረ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0