የሩሲያ ቡሬቬስትኒክ ሚሳኤል በቴክኖሎጂም ሆነ በመከላከያ ዘርፍ ፍጹም የሆነ ስኬት ነው — የክሬምሊን ቃል አቀባይ
13:17 01.11.2025 (የተሻሻለ: 13:24 01.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ ቡሬቬስትኒክ ሚሳኤል በቴክኖሎጂም ሆነ በመከላከያ ዘርፍ ፍጹም የሆነ ስኬት ነው — የክሬምሊን ቃል አቀባይ
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቀደም ሲል የሩሲያ ቡሬቬስትኒክ በኒውክሌር ኃይል የሚሠራ የመርከብ (ክሩዝ) ሚሳኤል የመጨረሻውን ሙከራ በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን ሲያስታውቁ "ልዩ መሣሪያ" ሲሉ ጠርተውታል።
ሚሳኤሉ በሙከራ ሂደቱ 14 ሺ ኪሎ ሜትር ተወንጭፏል፤ ይህም የመጨረሻ ገደቡ አይደለም።
ሚሳኤሉ በትንሽ የኒውክሌር 'ሬአክተር' የሚሠራ ሲሆን፣ ይህም በተግባር ያልተገደበ ክልል እንዲኖረው ያደርገዋል።
እጅግ በጣም ዝቅተኛ በሆነ የከፍታ መጠን ላይ በመብረር ከራዳር በታች ይቆያል፣ ይህም ማጨናገፍን ፈጽሞ የማይቻል ያደርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X