በኢራን እና እስራኤል ግጭት ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎች፦

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱበኢራን እና እስራኤል ግጭት ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎች፦
በኢራን እና እስራኤል ግጭት ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎች፦ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.06.2025
ሰብስክራይብ

በኢራን እና እስራኤል ግጭት ዙሪያ ወቅታዊ መረጃዎች፦

ኢራን-እስራኤል የሚያከናወኑት የአየር ጥቃት ስምንተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል። ዛሬ የተሠሙ ዜናዎች፦

🟠 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ ላይ የተካሄደው የግድያ ሙከራ መክሸፉን አማካሪያቸው ሞሃመድ ሆሴን ራንጅባራን ተናግረዋል።

🟠 እስራኤል ቴህራን ውስጥ የኢራን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ፕሮግራም አካል የሆነውን የመከላከያ ፈጠራና ምርምር ድርጅት ሕንፃ መታለች።

🟠 የግጭት አፈታት ምክር ቤት አባል ሞህሰን ረዛኢ ኢራን ሁሉንም የበለፀጉ የኒውክሌር ቁሳቁሶቿን ወደ አስተማማኝ ቦታዎች ማዛወሯን ተናግረዋል።

🟠 እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሜናዊ ኢራን ተቋማትን በመደብደብ የአየር ጥቃቶቿን ወሰን አስፍታለች። የኢራን መንግሥት ቴሌቪዥን አይአርአይቢ እንደዘገበው ከሆነ በካስፒያን ባሕር ዳርቻ የሰፊድሩድ ክልል ውስጥ የሚገኝ አንድ የኢንዱስትሪ ኮምፕሌክስ ተመትቷል።

🟠 በራሽት እና ከቴህራን በስተሰሜን በሚገኘው ላቫሳን ክልል ከፍተኛ ፍንዳታዎች እና ጥቃቶች ተመዝግበዋል።

ኢራን የመታቻቸው ቦታዎች የትኞቹ ናቸው?

🟠 ኢራን በደርዘን የሚቆጠሩ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል የተለያዩ አካባቢዎች አስወንጭፋለች፤ ከእነዚህም መካከል በደቡብ እስራኤል ቤርሼባ ከተማ እና ቴል አቪቭ ይገኙበታል።

🟠 የኢራን ሚሳኤል ምንም አይነት የማክሸፍ ሙከራ ሳይደረግ ቤርሼባን በቀጥታ በመምታት የመኖሪያ ሕንፃዎችን እንዳወደመ እና የማይክሮሶፍት ቢሮ በሚገኝበት የቴክኖሎጂ ፓርክ አቅራቢያ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱ ተገልጿል፡፡

🟠 ኢራን በኔጌቭ በረሃ በሚገኘው የኔቫቲም አየር ማዕከል ላይ ከፍተኛ የሚሳኤል ጥቃት እንደሰነዘረች ተዘግቧል። የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ሚሳኤሎቹ ከተወነጨፉ በኋላ በመላው ደቡባዊ እስራኤል የአየር ወረራ ማስጠንቀቂያዎች እንደተላለፉ አረጋግጧል፡፡

🟠 ኢራን በዌይዝማን የሳይንስ ተቋም ላይ ባደረሰችው ቀጥተኛ ጥቃት ጉዳት ደርሶበታል፡፡ ታይምስ ኦፍ እስራኤል እንደዘገበው ጥቃቱ በሁለት ህንፃዎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን አርባ አምስት ላቦራቶሪዎችም ተጠቅተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0