ብራዚል እና ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የግብርና ትብብራቸውን እያሳደጉ ነው ተባለ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱብራዚል እና ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የግብርና ትብብራቸውን እያሳደጉ ነው ተባለ
ብራዚል እና ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የግብርና ትብብራቸውን እያሳደጉ ነው ተባለ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.06.2025
ሰብስክራይብ

ብራዚል እና ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የግብርና ትብብራቸውን እያሳደጉ ነው ተባለ

ከአንድ ወር በፊት በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል የተፈረመው የግብርና ትብብር ስምምነት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር እና የጋራ ምርምርን ለማበረታታት ያለመና በብሪክስ ማዕቀፍ ያለውን ሰፊ ትብብር የሚያንፀባርቅ እንደሆነ በኢትዮጵያ የብራዚል ኤምባሲ የግብርና ጉዳዮች ኃላፊ ፋቢያና ቪላ አልቬስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ብራዚል በግብርና ላይ የተመሠረተውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የሞቃታማ አካባቢዎችን ምርታማነትን የሚያጎለብቱ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማጋራት ልታግዝ እንደምትችል ገልፀዋል፡፡

አልቬስ የኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ እድገት እና የብሪክስ አባልነት በማውሳት፤ የብራዚልን ዘላቂ ትብብር የማጎልበት ፍላጎት ገልጸዋል።

አክለውም በተለይ ሻንጋይ መቀመጫውን ያደረገው የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ የዓለምን ረሃብ በመዋጋት ረገድ ወሳኝ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ጠቁመዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0