የአርሜኒያ ሐዋርያዊ ቤተ ክርስቲያን ደጋፊ ሳምቬል ካራፔትያንን ለማሰር የአርሜኒያ ባለሥልጣናት የወሰዱትን ውሳኔ ጠበቃው አወገዙ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱየአርሜኒያ ሐዋርያዊ ቤተ ክርስቲያን ደጋፊ ሳምቬል ካራፔትያንን ለማሰር የአርሜኒያ ባለሥልጣናት የወሰዱትን ውሳኔ ጠበቃው አወገዙ
የአርሜኒያ ሐዋርያዊ ቤተ ክርስቲያን ደጋፊ ሳምቬል ካራፔትያንን ለማሰር የአርሜኒያ ባለሥልጣናት የወሰዱትን ውሳኔ ጠበቃው አወገዙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.06.2025
ሰብስክራይብ

የአርሜኒያ ሐዋርያዊ ቤተ ክርስቲያን ደጋፊ ሳምቬል ካራፔትያንን ለማሰር የአርሜኒያ ባለሥልጣናት የወሰዱትን ውሳኔ ጠበቃው አወገዙ

ነጋዴው ሰው ምንም ምክንያት ሳይኖር ለሁለት ወራት ታስረዋል። በዚህ አመክንዮ መሠረት ማንኛውም ሰው ሊታሰር ይችላል ሲሉ አርመን ፌሮያን ከፍርድ ቤት ውጭ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ስለ ጉዳዩ እስካሁን የታወቁት ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፦

▪ሳምቬል ካራፔትያን ሩሲያዊ ነጋዴ ናቸው።

▪የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በአርሜኒያ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሱ ያሉትን ጥቃት በመቃወም ለቤተ ክርስቲያኒቱ ድጋፋቸውን ገልጸዋል።

▪ማክሰኞ የአርሜኒያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የሬቫን በሚገኘው የካራፔትያን ቤት ውጭ እርምጃው መወሰዱን አስታውቋል።

▪ ደጋፊዎች እና የቅርብ ቤተሰቦች ተሰባስበው የነበረ ሲሆን ከ50 በላይ ሰዎች ታስረዋል።

▪ነጋዴው በፖሊስ መኪና ከቤታቸው ተወስደዋል።

▪ሰኞ ጠዋት ካራፔትያን ወደ አርሜኒያ የምርመራ ኮሚቴ ከተወሰዱ በሗላ ክስ እንደተከፈተባቸው ሚዲያዎች ዘግበዋል።

▪ባለሥልጣናቱ የአርሜኒያን መንግሥት ለመገልበጥ አነሳስተዋል የሚል ክስ አቅርበዋል፡፡

▪የእስር ውሳኔው ሙሉ በሙሉ ሕገ-ወጥ ነው ሲሉ ጠበቃው ሊያና ጋስፓሪያን ተናግረዋል።

▪የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒኮል ፓሺንያን በካራፔትያን ባለቤትነት የተያዘውን ኤሌክትሪክ ኔትወርክስ ኦፍ አርሜኒያ ኩባንያ በመንግሥት እንዲያዝ ጠይቀዋል።

▪የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ሞስኮ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለች እንደሆነ እና ለነጋዴው አስፈላጊው እገዛ እንደሚደርግ ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0