ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገልፃለች፦ ቁልፍ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?
11:50 11.06.2025 (የተሻሻለ: 12:04 11.06.2025)
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገልፃለች፦ ቁልፍ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሩሲያ ከኢትዮጵያ ጋር የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስር ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላት ገልፃለች፦ ቁልፍ ዘርፎች የትኞቹ ናቸው?
የሁለቱ ሀገራት የንግድ ማሕበረሰብ ተወካዮች ሰኔ 3 በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ውስጥ ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይ በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ገነት ተሾመ በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት አፅንዖት በመስጠት፤ የኢትዮጵያን የንግድና ኢንቨስትመንት አቅም አጉልተው አሳይተዋል።
የውይይቱ ዋና ዋና ጉዳዮች፦
🟠የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ማሻሻያዎች፣ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና ለንግድ ምቹ የሆኑ ፖሊሲዎች፣
🟠በዘርፍ-ተኮር የእድገት መስኮች ማዕድን፣ ቡና፣ አበባ፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ኢነርጂ ይገኙበታል።
በርካታ የሩሲያ ኩባንያዎች ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ያሳዩባቸው ዘርፎች፦
🟠የማዳበሪያ ምርት፣
🟠የግንባታ እቃዎች፣
🟠የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መገጣጠሚያ፣
🟠የፀሐይ ኃይል፣
🟠ማዕድንና ነዳጅና ጋዝ፣
🟠ምግብ ማቀነባበር።
ውይይቱ ከቢዝነስ ሩሲያ የሕዝብ ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
