የአፍሪካ አገራት በየዓመቱ እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር በምንዛሬ ልውውጥ ኪሳራ ያጋጥማቸዋል – ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ አገራት በየዓመቱ እስከ 5 ቢሊዮን ዶላር በምንዛሬ ልውውጥ ኪሳራ ያጋጥማቸዋል – ባለሙያ

 

በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን የአፍሪካ ንግድ ፖሊሲ ማዕከል አስተባባሪ ፕ/ር መላኩ ደስታ ለስፑትኒክ እንዳብራሩት፣ በአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መረጃ መሠረት አኅጉሪቱ በየዓመቱ በምንዛሬ ልውውጥ ሂደት ከፍተኛ ወጪ እያወጣች ትገኛለች።

 

አስተባባሪው የአፍሪካ አገራት በራሳቸው ገንዘቦች ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችለው የፓን-አፍሪካ የክፍያ ሥርዓት (ፓፕስ) ይህንን ወጪ ለመቀነስና የአኅጉሪቱን የውስጥ ንግድ ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።

 

"ይህንን መካከለኛ ሂደት በማስወገድ፣ አፍሪካ ከፍተኛ መጠን ያለውን ገንዘብ መቆጠብ እንደምትችል እናምናለን" ሲሉ ፕ/ር መላኩ፣ በአዲስ አበባ ከተካሄደው 2ኛው የፓን-አፍሪካ የክፍያ ሥርዓት ኮንፈረንስ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0