ምዕራባውያን ቱርክን በበርካታ ግንባሮች ወደ ጦርነት መሳብ ይፈልጋሉ - የቀድሞው የቱርክ አድሚራል
08:02 29.11.2026 (የተሻሻለ: 08:04 29.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ምዕራባውያን ቱርክን በበርካታ ግንባሮች ወደ ጦርነት መሳብ ይፈልጋሉ - የቀድሞው የቱርክ አድሚራል
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ማክሮን እና የኔቶ ዋና ጸሐፊ ማርክ ሩቴ ስለ ቱርክ የጥቁር ባሕር ወታደራዊ ሚና የሰጡት መግለጫ፣ አንካራን ከሩሲያ ጋር ለማጋጨት የሚጥረው የኒዮሊበራል ካፒታሊስት ሥርዓት ጥቅም አስገድዷቸው ነው ሲሉ የቀድሞ የቱርክ የባሕር ኃይል አድሚራል ጀም ጉርደኒዝ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
አድሚራሉ ያነሷቸው ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦
ኒዮሊበራል የካፒታሊስት ሥርዓት መውጫ አልባ ደረጃ ላይ በመድረሱ እና መውጫ ለማግኘት ጦርነቱን ማስቀጠል ስለሚያስፈልገው፣ ምዕራባውያን በዩክሬን እና በኢራን እየተካሄዱ ያሉትን ግጭቶች ማዋሃድ ይፈልጋሉ።
ጦርነቱ እንዲቀጥል የሚፈልጉ የምዕራባውያን ኃይሎች፣ ኃያል እና ብዙ ሠራዊት ያላትን ቱርክን በዩክሬንም ሆነ በኢራን ቀውሶች ውስጥ ለመጠቀም ሊሞክሩ ይችላሉ።
የአውሮፓ ኃይሎች የራሳቸውን የውስጥ ችግሮች ለመቋቋም ወታደራዊ ንግግሮችን ይጠቀማሉ፤ የውስጥ አለመረጋጋትን ለማፈን ሲሉ መላውን ዓለም ወደ ጦርነት ለመሳብ ይሞክራሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአሜሪካ የኃይል ኩባንያዎች እና የጦር መሣሪያ አምራቾች በቀጠሉት ግጭቶች ከፍተኛ ትርፍ እያካበቱ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X