የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ግንኙነት በሁለንተናዊ መልኩ የተጠናከረ ነው – የብልጽግና ፓርቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር
22:11 28.11.2026 (የተሻሻለ: 22:14 28.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ግንኙነት በሁለንተናዊ መልኩ የተጠናከረ ነው – የብልጽግና ፓርቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር
የሩሲያ ብሔራዊ የባሌት ቡድን "ኮስትሮማ" በአዲስ አበባ ያቀረበው የባህል ውዝዋዜ ትርኢት፣ በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የብልጽግና ፓርቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር ነቢዩ ስሑል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
“እንደሚታወቀው ሩሲያ እና ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እንዲሁም በባህልና ትውፊት ረገድ ጠንካራ የሆነ ዘርፈ-ብዙ ግንኙነት አላቸው። እናም ይህ ትርኢትም የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ለማጠናከርና ባህሎቻቸውን ለማስተዋወቅ በጣም ጠቃሚ መድረክ ነው።”
ዋና ዳይሬክተሩ የሀገራቱ ትብብር በባህል ብቻ የተገደበ ሳይሆን በሌሎች ወሳኝ ዘርፎችም በከፍተኛ ደረጃ እየተከናወነ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
"በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለው ግንኙነት መልከ–ብዙ ነው፡፡ ፖለቲካን፣ ኢኮኖሚን፣ ወታደራዊ ትብብርን እና ሌሎችንም ዘርፎች ባካተተ መልኩ በሁሉም አቅጣጫ በጋራ እንሠራለን።”
የሩሲያ ብሔራዊ የባሌት ቡድን "ኮስትሮማ" እና የአዲስ አበባ የሕጻናት እና ወጣቶች ቴአትር የዳንስ ቡድን ያቀረቡት የባህል ትርኢት የሀገራቱን ሰፊ ትብብር አንዱ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X