አፍሪካ በፍራፍሬ ማቀነባበር እና ማቆየት ዘርፍ የሩሲያን ልምድ ትሻለች - የአፍሪካ ቢዝነስ ክለብ ፕሬዝዳንት

© telegram sputnik_ethiopiaአፍሪካ በፍራፍሬ ማቀነባበር እና ማቆየት ዘርፍ የሩሲያን ልምድ ትሻለች - የአፍሪካ ቢዝነስ ክለብ ፕሬዝዳንት
አፍሪካ በፍራፍሬ ማቀነባበር እና ማቆየት ዘርፍ የሩሲያን ልምድ ትሻለች - የአፍሪካ ቢዝነስ ክለብ ፕሬዝዳንት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 28.11.2026
ሰብስክራይብ

አፍሪካ በፍራፍሬ ማቀነባበር እና ማቆየት ዘርፍ የሩሲያን ልምድ ትሻለች - የአፍሪካ ቢዝነስ ክለብ ፕሬዝዳንት

የሩሲያ እና የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ከንግድ ልውውጥ ባለፈ የሩሲያ ኩባንያዎች በአኀጉሪቱ የጋራ ንግድ ድርጅቶችን በማቋቋም እና ምርቶችን በአገር ውስጥ በማምረት ላይ ሊያተኩር ይገባል ሲሉ በሩሲያ የአፍሪካ ቢዝነስ ክለብ ፕሬዝዳንት ሉዊስ ጉዌንድ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በቂ የማቀነባበሪያ እና የማቆያ አቅም ባለመኖሩ ምክንያት በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ቶን ፍራፍሬ፣ ማለትም ከአፍሪካ አጠቃላይ ምርት እስከ 50 በመቶ የሚደርሰው በምርት ስብሰባ ወቅት እንደሚባክን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ በተለይም የፍራፍሬ ጭማቂዎችን፣ "ኮምፖቶችን"፣ ማርማላታዎችን እና የታሸጉ ምግቦችን ማምረት ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቱ የጠቀሷቸው የሚያስፈልጉ መሠረተ ልማቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

⏺ የመጋዘኖች ግንባታ፣

⏺ የማቀነባበሪያ መሳሪያዎች አቅርቦት፣

⏺ የማቀዝቀዣ እና የማበረጃ ሥርዓቶች ተከላ፣

⏺ የኤሌክትሪክ ኃይል መሠረተ ልማት ማስፋፋት እንዲሁም

⏺ የመንገድ ግንባታ ይገኙበታል።

የሩሲያ ኩባንያዎች የተዘጋጁ ምርቶችን ከመግዛት ይልቅ በቀጥታ በአፍሪካ የሻይ እና የቡና እርሻዎች ላይ ኢንቨስት ማድረጋቸው የበለጠ አትራፊ ሊሆንላቸው እንደሚችልም ጉዌንድ አክለው ገልጸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0