የሩሲያው "ኮስትሮማ" ብሔራዊ የባሌት ቡድን በአዲስ አበባ የሕጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ባሕላዊ ዳንስ እያቀረበ ነው

ሰብስክራይብ

የሩሲያው "ኮስትሮማ" ብሔራዊ የባሌት ቡድን በአዲስ አበባ የሕጻናት እና ወጣቶች ቴአትር ባሕላዊ ዳንስ እያቀረበ ነው

 

በዓለም ዙሪያ ከ7 ሚሊዮን በላይ ተመልካቾችን ያስደመመው የሩሲያ ብሔራዊ የባሌት ቡድን "ኮስትሮማ" የኢትዮ-ሩሲያን የባሕል ትስስር የሚያደምቅ ታላቅ ትርኢት እያካሄደ እንደሚገኝ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

“የሩሲያ ብሔራዊ የዳንስ መድረክ፤ የታላቋ ሀገር ታላቅ ታሪክ” በተሰኘው ታላቅ የሙዚቃ እና ውዝዋዜ ምሽት ላይ የመንግሥት ተወካዮች፣ የኪነ–ጥበብ እና የሙዚቃ ባሙያዎች እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ዝግጅቱን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፍጹም ዘገዬ፣ በዝግጅቱ ላይ 50 ያህል የሩሲያ የባሕል ተወዛዋዦች እንደሚሳተፉ ጠቁመው፤ የቴአትር ቤቱ ተወዛዋዦችም ከወራት በኋላ በሩሲያ ተመሳሳይ ዝግጅት እንደሚያቀርቡ አስታውቀዋል።

የሩሲያ ብሔራዊ የባሌት ቡድን የሌና ሳሬምኮ በበኩላቸው፣ የባሕል ልውውጡ የሚካሄደው የረጅም ዘመን ጠንካራ ግንኘነት ባላቸው እና በብዝኃ-ባሕል በበለጸጉ ሁለት ሀገራት መካከል መሆኑ ትርጉሙ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል።

"እዚህ ያለነው የእኛን ባሕል ለማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያም በቅርበት ለማወቅ ነው" ብለዋል።

የሁለቱም ሀገራት ተወዛዋዦች የሚሳተፉበት ተመሳሳይ ዝግጅት ነገ ሕዳር 20 ቃን 23019 ዓ.ም በአድዋ ድል መታሰቢያ እንደሚካሄድ ተናግረዋል።

የሩሲያ የሳይንስ እና የባህል ማዕከል በአዲስ አበባ ዋና ዳይሬክተር ቭላዲሚር ጎሎቫቼቭ በበኩላቸው፣ ዝግጅቱ የባሕል ትስስርን ከማጠናከር ባለፈ በሁለቱ ሀገራት መካከል የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር እና የከነ ጥበብ ዘርፍ ትብብርን ለማጠናከር እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0