"የአፍሪካ ሉዓላዊነት የባለቤትነት ጉዳይ ነው" ሲሉ ባለሙያው በአየር ንብረት እና በጤና ዘርፍ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቀረቡ
"የአፍሪካ ሉዓላዊነት የባለቤትነት ጉዳይ ነው" ሲሉ ባለሙያው በአየር ንብረት እና በጤና ዘርፍ ተግባራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ አቀረቡ
የአየር ንብረት ለውጥ በጤና ላይ በሚያደርሰው ተጽዕኖ እና ለዘርፉ በሚመደበው የፋይናንስ ድጋፍ መካከል ሰፊ ክፍተት መኖሩን እና ከአየር ንብረት ፋይናንስ ውስጥ ወደ ጤና ዘርፍ የሚሄደው 6 በመቶ ያህሉ ብቻ መሆኑን የወባ በሽታን ለማጥፋት የተቋቋመው የአር.ቢ.ኤም አጋርነት ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማይክል አዴኩንሌ ቻርልስ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል፡፡
የወባ በሽታ በአፍሪካ ላይ እያደረሰ ያለው አስከፊ ጉዳት
ለአብነት ያህል፣ የወባ በሽታ በየዓመቱ 620 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት እንደሚቀጥፍና ከዚህ ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ ሞት የሚከሰተው በአፍሪካ መሆኑን ስራ አስፈፃሚው በአዲስ አበባ ከተካሄደው 5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የኅብረተሰብ ጤና ጉባኤ ጎን ለጎን ተናግረዋል።
የሀብት ማሰባሰብ ጥሪ
የአየር ንብረት ለውጥ በጤና ላይ የሚያደርሰው ከፍተኛ ተጽዕኖ እና እየጨመረ የመጣው የጤና ጫና፣ ለዘርፉ ተጨማሪ ሀብት ማሰባሰብ እንደሚያስፈልግ በግልጽ ያሳያል ሲሉ ቻርልስ ገልጸዋል።
"በአንድ ድምፅ መናገር እንችላለን፤ የፋይናንስ ድጋፉን ማግኘት ከቻልን የሰዎችን ሕይወት ማዳን እንችላለን" ብለዋል።
የኮፕ 32 ዕድል
ኮፕ32 በአዲስ አበባ የሚካሄድ መሆኑን ተከትሎ፣ አፍሪካ አሁን እየተካሄዱ ባሉ የአየር ንብረት ድርድሮች ላይ በመመሥረት ተጨባጭ እርምጃ እንዲወሰድ፣ ሀብት እንዲመደብ እና በመላው አኀጉሪቱ ጠንካራ የጤና ሥርዓት እንዲገነባ ግፊት ለማድረግ ትልቅ ዕድል እንዳላት ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X