ኢትዮጵያ እንደ ሩሲያ እና ቻይና ካሉ ሀገራት ጋር በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ መሆኗ ለሕዋ ሳይንስ ዘርፏ “ትልቅ ዕድል ነው” – የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እንደ ሩሲያ እና ቻይና ካሉ ሀገራት ጋር በብሪክስ ማዕቀፍ ውስጥ መሆኗ ለሕዋ ሳይንስ ዘርፏ “ትልቅ ዕድል ነው”  – የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት

 

ኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነቷ ከሩሲያና ቻይና መሰል በሕዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የላቀ ልምድ ካካበቱ ሀገራት በርካታ ትምህርቶችን ልትወስድ እንደምትችል የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ይሹሩም ዓለማየሁ ገለጹ።

 

“ከእነዚህ ሀገራት ጋር አንድ ላይ በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ መሆናችን እንደ ታዳጊ ሀገር ለእኛ ትልቅ እድል ነው። ከአቅም ግንባታና ከሰው ኃይል ልማት እንዲሁም ከመሠረተ ልማት አንጻር ብዙ ልንማር እንችላለን” ብለዋል።

 

ዶ/ር ይሹሩም እንዳሉት፣ በሕዋ ዘርፍ የበለጸጉ ሀገራትን የልማት ጉዞና ያለፉባቸውን ፈተናዎች መመልከት ኢትዮጵያ የራሷን የሕዋ አቅም በተሻለ ፍጥነት እንድታሳድግ የሚያግዝ ተሞክሮ ነው።

 

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ በብሪክስ ማዕቀፍ ኢትዮጵያ ከሩሲያና ከቻይና ልትቀስማቸው ስለምትችላቸው ተሞክሮዎች ከ2ኛው የአዲስ ስፔስ ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ የሰጡትን ማብራሪያ በቪዲዮው ይመልከቱ።

 

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0