ኢትዮጵያ የራሷን የሳተላይት ማምጠቂያ መሠረተ ልማት ለመገንባት እየተዘጋጀች ነው - የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት
20:25 27.11.2026 (የተሻሻለ: 20:34 27.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ የራሷን የሳተላይት ማምጠቂያ መሠረተ ልማት ለመገንባት እየተዘጋጀች ነው - የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት
ኢትዮጵያ የሳተላይት ማምጠቂያ፣ መገጣጠሚያና ማሰባሰቢያ፣ ማቀናጀትና መፈተሻ (ኤአይቲ) መሠረተ ልማት ለመገንባት ያላትን ዕቅድ ወደ ተግባር ለማሸጋገር እየሠራች መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ይሹሩም ዓለማየሁ ገልጸዋል።
“የአዋጭነት ጥናት አከናውነናል። ከዚያ በተጨማሪ ወደ ተግባር ለመግባት በሂደት ላይ እንገኛለን። ከሮስኮስሞስ አንዱ ሆኖ ሌሎችንም ከሌሎችም ተቋማት ጋር ለመሥራት ክፍት ነን።
በአሁኑ ወቅት በዋናነት ከሩሲያ የመንግሥት የጠፈር ድርጅት ሮስኮስሞስ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር ይሹሩም አስረድተዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፣ ከ2ኛው የአዲስ ስፔስ ፎረም ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቆይታ ያነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች በቪዲዮ ይመልከቱ።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X