አዲስ አበባ የአፍሪካ የፋይናንስ ጥምረት ቋሚ መቀመጫ ልትሆን ነው
18:15 27.11.2026 (የተሻሻለ: 18:24 27.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አዲስ አበባ የአፍሪካ የፋይናንስ ጥምረት ቋሚ መቀመጫ ልትሆን ነው
የአፍሪካ ባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማት ጥምረት (አፍሪካ ክለብ) ቋሚ ጽሕፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ለማቋቋም ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የአስተናጋጅ ሀገር ስምምነት ተፈራርሟል። ስምምነቱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተፈረመ ሲሆን፣ ቋሚ ጽሕፈት ቤቱን በከተማዋ ለማቋቋምና ሥራውን ለማስተዳደር ሕጋዊ መሠረት ይፈጥራል።
የስምምነቱ ዋና ፋይዳዎች፦
አዲስ አበባ ለጥምረቱ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ ማዕከል ትሆናለች።
የአፍሪካን ካፒታል በማሰባሰብ ለአህጉሪቱ የልማት ቅድሚያዎች የሚውል የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ ያግዛል።
በአፍሪካውያን የሚመራና የአኅጉሪቱን ፍላጎቶች ያማከለ የፋይናንስ ሥርዓት ለመገንባት አስተዋጽኦ ያደርጋል።
ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ያለውን ቅርብ ትብብር በማጠናከር የአጀንዳ 2063 እና የአኅጉሪቱን ኢኮኖሚያዊ ውህደት ግቦች ለማሳካት ይረዳል።
አፍሪካ ክለብ በየካቲት 2016 ዓ.ም (የካቲት 2024) ከአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ጋር በመተባበር መመሥረቱ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X