የሩሲያ ቋንቋ የሥነ-ጽሑፍ ውድድር ከ69 ሀገራት የተውጣጡ 1,788 ሥራዎችን ሳበ
17:52 27.11.2026 (የተሻሻለ: 17:54 27.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የሩሲያ ቋንቋ የሥነ-ጽሑፍ ውድድር ከ69 ሀገራት የተውጣጡ 1,788 ሥራዎችን ሳበ
ከ69 ሀገራት በሩሲያ ቋንቋ በሚጽፉ ደራሲያን የቀረቡ 1,788 ሥራዎች የተሳተፉበት የሩስኪ ግላጎል (የሩሲያ ቃል) ዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ውድድር አሸናፊዎች በሞስኮ ይፋ ተደርገዋል።
ውድድሩ ዝርው ጽሑፍ፣ ግጥም፣ የሕፃናት ሥነ-ጽሑፍ፣ ድራማ፣ የሥነ-ጽሑፍ ሒስ፣ ትርጉም እና ታሪካዊ ትውስታን ጨምሮ ሰባት ዘርፎችን አካቷል።
በስድስቱ ዋና ዋና ዘርፎች አሸናፊዎች የተመረጡት በሁለት የዕድሜ ምድቦች ማለትም ዕድሜያቸው ከ35 ዓመት በላይ ለሆኑ ደራሲያን ማስተር እንዲሁም ከ18 እስከ 35 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ደግሞ ወጣት ደራሲ በሚል ተከፍሎ ነው።
የውድድሩ ባለሙያዎች የአሸናፊ ሥራዎችን ጥራትና ብዝኃነት እንዲሁም የሩሲያ ቋንቋ የተለያዩ ሀገራት ደራሲያንን በማገናኘት ረገድ ያለውን ሚና አጉልተው ገልጸዋል።
"ለፈጠራ ሥራዎቻቸው የሩሲያ ቋንቋን የመረጡ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሰዎች፣ ለሩሲያ፣ ለታላቁና ለሺህ ዓመታት ለዘለቀው ባሕሏ ባላቸው ፍላጎት እንዲሁም በወደፊት ዕጣ-ፈንታዋ ላይ ባላቸው እምነት አንድ ሆነዋል። ዛሬ ከመላው ዓለም የመጡ ሰዎች ወደ ሩሲያ ባሕል መሳባቸው በጣም አስፈላጊ ነው" ሲሉ የስቴት ዱማ ምክትል አባል ፒዮትር ቶልስቶይ ገልጸዋል።
በጥቅምት ወር ሩስኪ ግላጎል በ"የዓለም ቋንቋ" ዘርፍ ዓለም አቀፉን የኢዩኤሽያ ሽልማት አሸንፏል።
ሽልማቱን ያበረከቱት የአርቲ እና የሮሲያ ሴጎድኒያ (የስፑትኒክ እናት ተቋም) ዋና አዘጋጅ ማርጋሪታ ሲሞኒያን ናቸው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X