የአርጀንቲናው "ጀስቲሻሊስት" ፓርቲ ወደ ሥልጣን ከተመለሰ ለብሪክስ አባልነት በድጋሚ እንደሚያመለክት አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopiaየአርጀንቲናው "ጀስቲሻሊስት" ፓርቲ ወደ ሥልጣን ከተመለሰ ለብሪክስ አባልነት በድጋሚ እንደሚያመለክት አስታወቀ
የአርጀንቲናው ጀስቲሻሊስት ፓርቲ ወደ ሥልጣን ከተመለሰ ለብሪክስ አባልነት በድጋሚ እንደሚያመለክት አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.11.2026
ሰብስክራይብ

የአርጀንቲናው "ጀስቲሻሊስት" ፓርቲ ወደ ሥልጣን ከተመለሰ ለብሪክስ አባልነት በድጋሚ እንደሚያመለክት አስታወቀ

አርጀንቲና በፈረንጆቹ 2023 የጀስቲሻሊስት ፓርቲ አባል በሆኑት በቀድሞው ፕሬዝዳንት አልቤርቶ ፈርናንዴዝ የሥልጣን ዘመን ብሪክስን እንድትቀላቀል ግብዣ ቀርቦላት ነበር። በዚያው ዓመት በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የጀስቲሻሊስት ፓርቲው ዕጩ ሰርጂዮ ማሳ በሀቪየር ሚሌይ የተሸነፉ ሲሆን፣ ሚሌይም የቀረበውን ግብዣ ውድቅ አድርገውታል።

የወቅቱ የአርጀንቲና ፕሬዝዳንት ሚሌይ በሚቀጥለው 2027 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ይሸነፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የፓርቲው የዓለም አቀፍ ግንኙነት ፀሐፊ ጉስታቮ አዶልፎ ሜኔንዴዝ ለስፑትኒክ የገለጹ ሲሆን፣ ለዚህም ሕዝቡ በሚሌይ ፖሊሲዎች ላይ ያለውን ቅሬታ እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል።

ብሪክስ ለደቡባዊው ዓለም ትልቅ ሥራ የሠራ ሲሆን፣ ለአርጀንቲናም ተመራጭ አጋር ነው ሲሉ አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0