የሩሲያ የጦር መሣሪያ አምራች በሞስኮ በተካሄደው ኢንተርፖሊቴክስ ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ ላይ በተግባር የተፈተኑ ሁለት ጠመንጃዎችን አቀረበ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ የጦር መሣሪያ አምራች በሞስኮ በተካሄደው ኢንተርፖሊቴክስ ዓለም አቀፍ አውደ ርዕይ ላይ በተግባር የተፈተኑ ሁለት ጠመንጃዎችን አቀረበ

የመጀመሪያው 'ኤምቲኤስ572' የተሰኘው ባለ ትልቅ አፈ-ሙዝ ጠመንጃ መሆኑን የሩሲያ ማዕከላዊ የስፖርትና የአደን የጦር መሣሪያዎች ንድፍና ምርምር ቢሮ ተወካይ ሚካኤል ባዡቶቭ ከአውደ ርዕዩ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

የመሣሪያው መገለጫዎች፦

በፍጥነት የሚነቀል የድምፅ ማፈኛ፣

የሚስተካከል በጋዝ የሚሠራ ሥርዓት፣

ተነቃይ የጥይት ካዝና፣

የሚታጠፍና የሚስተካከል ሰደፍ።

ሁለተኛው መሣሪያ 'ኦኤስቪ-96' የተሰኘው ጠመንጃ ሲሆን እንደ ባዡቶቭ ገለጻ 'ዘመን የማይሽረው ክላሲክ' ነው።

ልዩ መገለጫዎቹ፦

ለማጓጓዝ ቀላል፣

ተነቃይ የጥይት ካዝና፣

ውጤታማ የጠመንጃውን ምት መቀነሻ።

የሁለቱንም መሣሪያዎች ተግባራዊ ማሳያ ለመመልከት በስፑትኒክ አፍሪካ የተዘጋጀውን ቪዲዮ ይመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0