- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ሽግግር፡- የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ አወጋገድ ስጋቶች

የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ሽግግር፡- የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ አወጋገድ ስጋቶች
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ካገደች ወዲህ፣ በአውቶሞቲቭ ገበያው ላይ ትልቅ መዋቅራዊ ለውጥ ታይቷል። ሆኖም ይህንን አረንጓዴ ሽግግር ዘላቂ ለማድረግ የፍላጎትና አቅርቦት ሚዛንን፣ የቻርጂንግ መሠረተ ልማቶችን፣ የተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪዎችን አዋጭነት እንዲሁም አገልግሎታቸውን የጨረሱ ባትሪዎችን አወጋገድ ስጋት በጥልቀት መፈተሽ ይገባል።” —

ፋኑኤል ኃይሌ፣ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አማካሪ፣ የገበያ ባለሙያ እና በታምሪን ሞተርስ የንግድ ኦፕሬሽን ዋና ኃላፊ

ወቅታዊና ወሳኝ አጀንዳ በሚዳሰስበት በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦

“የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ሽግግር፡ የኤሌክትሪክ እና የተፈጥሮ ጋዝ ተሽከርካሪዎች ገበያ፣ ተግዳሮቶች እና አገልግሎታቸውን የጨረሱ ባትሪዎች አወጋገድ ስጋቶች” በሚል ርዕስ፣ የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ አማካሪ፣ የገበያ ባለሙያ እና በታምሪን ሞተርስ የንግድ ኦፕሬሽን ዋና ኃላፊ ከሆኑት ከአቶ ፋኑኤል ኃይሌ ጋር ሦስት ዐበይት ምሰሶዎችን በጥልቀት እንቃኛለን፦

የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EV) ወቅታዊ የፍላጎትና አቅርቦት ሚዛን፣ የዋጋ ተመጣጣኝነት፣ የመለዋወጫና የኃይል መሙያ ጣቢያዎች እጥረት፤

ሀገሪቱ ያላትን የተፈጥሮ ጋዝ ሀብት በመጠቀም በተፈጥሮ ጋዝ (CNG/LNG) የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች በተለይም ለከባድ የጭነት እና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ያላቸውን አዋጭነት፤

የኢቪ ባትሪዎች የአገልግሎት ዘመን ሲያበቃ በአካባቢ እና በህብረተሰብ ጤና ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ኬሚካላዊና የእሳት አደጋ ስጋቶች ላይ በስፋት ተወያይተንበታል።

🔊 ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡ ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0