ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በመከላከያ እና በአቪዬሽን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በመከላከያ እና በአቪዬሽን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ
ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በመከላከያ እና በአቪዬሽን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.11.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ፓኪስታን በመከላከያ እና በአቪዬሽን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ስምምነቱ የተደረሰው በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዑመር ሁሴን እና የፓኪስታን ፌዴራል መከላከያ ሚኒስቴር ዋና ጸሐፊ ሌተናል ጄኔራል መሐመድ አሊ በራዋልፒንዲ ባደረጉት ከፍተኛ ውይይት መሆኑን በኢስላማባድ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል።

የውይይቱ ቁልፍ ነጥቦች፦

◻ ሁለቱ ወገኖች በቀጣናዊ የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች እንዲሁም በመከላከያ እና በአቪዬሽን መስኮች ያላቸውን አጋርነት ማስፋት በሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ መንገዶች ዙሪያ በስፋት መክረዋል።

◻ አምባሳደር ዑመር ሁሴን፤ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ፣ በአቪዬሽን፣ በቱሪዝም እና በባህል ዘርፎች ያለውን ትብብር በማጎልበት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

◻ የፓኪስታን የመከላከያ ዋና ጸሐፊ በበኩላቸው፤ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሳደግ ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0