ታንዛኒያ የተሽከርካሪዎች መከታተያ ሥርዓትን ወደ ትምህርት ቤት አውቶቡሶች፣ የጭነት መኪናዎች እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ልታስፋፋ ነው - መገናኛ ብዙኃን
16:20 26.11.2026 (የተሻሻለ: 16:24 26.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታንዛኒያ የተሽከርካሪዎች መከታተያ ሥርዓትን ወደ ትምህርት ቤት አውቶቡሶች፣ የጭነት መኪናዎች እና ሌሎች ተሽከርካሪዎች ልታስፋፋ ነው - መገናኛ ብዙኃን
የተሽከርካሪዎች መከታተያና መቆጣጠሪያ ሥርዓት በቀድሞው የተሽከርካሪዎች መከታተያ ሥርዓት ላይ የነበሩ ድክመቶችን እንደሚቀርፍ የታንዛኒያ የየብስ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አብደላህ ምሃጋማ ተናግረዋል።
ሥርዓቱ ተጠቃሚዎች የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ መረጃዎችን እንዲያዛቡ የሚያስችሉ ክፍተቶችን እንደሚያካትት ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።
አዲሱ ሥርዓት የቪዲዮ ቴሌማቲክስን የሚያስተዋውቅ ሲሆን ወደ አሽከርካሪው የሚያዩ እንዲሁም የተሽከርካሪዎችን የፊትና የጎን ክፍሎች የሚሸፍኑ ካሜራዎች የአሽከርካሪውን ባሕርይ ለመቆጣጠርና አደገኛ ልማዶችን ለመለየት ጥቅም ላይ ይውላሉ፦
የደህንነት ቀበቶ አለማሰር፣
እያሽከረከሩ ተንቀሳቃሽ ስልክ መጠቀም፣
የአሽከርካሪው የድካም ምልክቶች።
ይህ እርምጃ አፍሪካ ውስጥ ተከታታይ ገዳይ የአውቶቡስ አደጋዎች መከሰታቸውን ተከትሎ የመጣ ነው። በመስከረም ወር በኬፕ ቨርዴ በአውቶቡስና የጭነት መኪና ግጭት ቢያንስ 20 ሰዎች ሲሞቱ፤ በሐምሌ ወር ደግሞ በኡጋንዳ በደረሰ የትምህርት ቤት አውቶቡስ የመከስከስ አደጋ 20 ሕፃናትና አንድ አዋቂ ሞተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X