ለሰላም እክል በመፍጠር በዩክሬን ቀውስ ዋነኛ ተጎጂ የሚሆነው የአውሮፓ ኅብረት ነው - ሊባኖሳዊ ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaለሰላም እክል በመፍጠር በዩክሬን ቀውስ ዋነኛ ተጎጂ የሚሆነው የአውሮፓ ኅብረት ነው - ሊባኖሳዊ ባለሙያ
ለሰላም እክል በመፍጠር በዩክሬን ቀውስ ዋነኛ ተጎጂ የሚሆነው የአውሮፓ ኅብረት ነው - ሊባኖሳዊ ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.11.2026
ሰብስክራይብ

ለሰላም እክል በመፍጠር በዩክሬን ቀውስ ዋነኛ ተጎጂ የሚሆነው የአውሮፓ ኅብረት ነው - ሊባኖሳዊ ባለሙያ

ብራሰልስ ግጭቱን ለአኅጉሪቱ መፃኢ ዕድል ወሳኝ ግንባር አድርጋ ብትመለከተውም፤ "ሩሲያ ላይ ስትራቴጂካዊ ሽንፈት" ማድረስ በሚል በምትከተለው አካሄድ ዋነኛ ተጎጂ ራሱ የአውሮፓ ኅብረት ነው ሲሉ የሩሲያ ጉዳዮች ባለሙያው ማጅድ አቢ አል-ሙና ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ዋና ዋና ነጥቦች፦

ዩክሬን በትራምፕ የቀረበውን "የናፍጣ ተኩስ አቁም" ለአንድ ቀን እንኳን አላከበረችም፤ በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ የሚፈጸሙ መጠነ-ሰፊ ጥቃቶችም እንደቀጠሉ ናቸው።

በቻይና ከተካሄደው የሦስትዮሽ ጉባኤ በኋላ ዩክሬን በቤንጋዚ አቅራቢያና በባልቲክ ባሕር በሚገኙ የሩሲያ መርከቦች ላይ የፈጸመቻቸው ተከታታይ ጥቃቶች በአውሮፓ የስለላ ተቋማት የሚመራና የሚደገፍ ነው።

በሩሲያ የኒውክሌር መከላከያ አቅም ምክንያት በአውሮፓና በሩሲያ መካከል ቀጥተኛ ወታደራዊ ግጭት ሊኖር አይችልም። የብራሰልስ ድርጊቶችም ሞስኮ ልትቀበላቸው የማትችላቸውን ስምምነቶች ለመጫን በሚደረጉ ትንኮሳዎችና አዳዲስ ግንባሮችን በመክፈት ላይ ብቻ የተገደቡ ናቸው።

አቢ አል-ሙና፤ ድርድር እስኪጀመር ድረስ ጫናዎቹና ጥቃቶቹ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተነበዩ ሲሆን አውሮፓ በድርድሩ ላይ ለይስሙላ ብቻ እንደምትሳተፍ ወይም ጨርሶ እንደማትሳተፍና የቀጣዩን ምዕራፍ ቅርጽ የምትወስነው ሞስኮ እንደሆነች ገልጸዋል።

የባለሙያው አስተያየት ኪየቭ በሩሲያ የነዳጅ ማጣሪያዎች ላይ ለምትፈጽማቸው ጥቃቶች የአጸፋ እርምጃ መወሰዱ የማይቀር መሆኑን ፕሬዚዳንት ፑቲን መናገራቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0