ሩሲያ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የሚታገዝ አዲስ የፀረ-ድሮን መሣሪያ ይፋ አደረገች

ሰብስክራይብ

ሩሲያ በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የሚታገዝ አዲስ የፀረ-ድሮን መሣሪያ ይፋ አደረገች

የአዲሱ ሥርዓት ዋና አካል 12.7 ሚሊ ሜትር የሆነ ኮርድ ከባድ መትረየስ የተገጠመለትና በመጀመሪያ ለባሕር ኃይል መርከቦች ተብሎ የተዘጋጀው ነው።

ይህ የውጊያ መሣሪያ በሰከንድ እስከ 80 ሜትር ፍጥነት የሚበሩ የአየር ዒላማዎችን መከታተልና ማጥቃት የሚችል ሲሆን ከአብዛኞቹ ባለ ቋሚ ክንፍ የረጅም ርቀት ድሮኖች የበረራ ፍጥነት በላይ ነው።

ሰው ሠራሽ አስተውህሎቱ ዒላማዎችን በራሱ እንዲለይ፣ አሳሳች ምልክቶችን ችላ እንዲል፣ የጠላትን የስጋት ደረጃ እንዲመዝን እንዲሁም ለባለስቲኩ አዲስ አቅጣጫ እንዲያሰላ ያስችለዋል።

አንድ ኦፕሬተር እስከ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆኖ በርቀት መቆጣጠሪያ ከ4 እስከ 16 የሚደርሱ የመሣሪያ ሥርዓቶችን ማንቀሳቀስ ይችላል።

በሮስቴክ ንዑስ ኩባንያ ኡራልቫጎንዛቮድ የተነደፈው ይህ አዲስ መሣሪያ፤ በሞስኮ በተካሄደው ኢንተርፖሊቴክስ-2026 ዓለም አቀፍ የመንግሥት ደህንነት መሣሪያዎች አውደ ርዕይ ላይ ለዕይታ ቀርቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0