ከፖለቲካዊ ነፃነት ባሻገር ያለው የአፍሪካ ኢኮኖሚያዊ፣ የገንዘብ እና የእውቀት ሉዓላዊነት ትግል፤ ሀገር በቀል ሳይንስ
19:03 25.11.2026 (የተሻሻለ: 19:03 26.11.2026)
የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ትራንስፖርት ሽግግር፡- የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪ አወጋገድ ስጋቶች
ሰብስክራይብ
“የብሪክስ ሀገራት ተሰባስበው በብዙ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው። የብሪክስ አካዳሚዎች ማህበር፣ የሳይንስ ማህበራት እና ሌሎችም አሉ። ይህ ደግሞ የበለጠ መቀጠል አለበት። አሁን ያለው ገና በጅማሮ ወይም በጨቅላነት ደረጃ ላይ ነው። ይህ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ማደግ እና ወደ ተግባር መለወጥ ይኖርበታል።” ሲሉ ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ሁለት ዐበይት ጉዳዮች በሚዳሰሱበት በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን፦ በክፍል አንድ፦ “አፍሪካ፡ ፖለቲካዊ ነፃነት ከኢኮኖሚያዊ፣ ከገንዘብ እና ከእውቀት (Epistemic) ጥገኝነት አንጻር” በሚል ርዕስ፣ መደበኛ የፖለቲካ ነፃነት ከታወጀ አሥርት ዓመታት ቢያልፉም አህጉሪቱን አሁንም ተብትበው የያዟትን የውጭ ኢኮኖሚያዊ መዋቅሮች፣ የገንዘብ ሥርዓት ጫናዎች እና የእውቀት ጥገኝነትን በመስበር እውነተኛ ሉዓላዊነትን ስለማረጋገጥ በሊንከን ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና የፓን-አፍሪካ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር፣ ጸሐፊ እና የፖለቲካ ተንታኝ ፕሮፌሰር ግናኬ ላጎኬ ጋር የተወያየንበት ሲሆን፤
በክፍል ሁለት፦ “ሀገር በቀል ሳይንስ፦ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና የወደፊቱ የእውቀት አመራር” በሚለው ርዕስ፣ የሀገር በቀል እውቀትና ሳይንስ ለዘላቂ ልማት ያለውን ፋይዳ፣ ባህላዊ እውቀቶችን በዘመናዊ ሳይንስ የማበልጸግ ሂደትን እንዲሁም በብሪክስ (BRICS+) ማዕቀፍ ውስጥ እየተጠናከረ የመጣውን የሳይንስ ትብብር የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ከሆኑት ከፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ ጋር በጥልቀት እንቃኘዋለን።
🔊 ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox