- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ቴክኖሎጂን በአፍሪካ፣ ለአፍሪካ መሥራት

ቴክኖሎጂን በአፍሪካ፣ ለአፍሪካ መሥራት
ሰብስክራይብ
የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የ2026 ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ባለፉት 25 ዓመታት የአፍሪካ የነፍስ ወከፍ የማኑፋክቸሪንግ እሴት ጭማሪ በዓመት በአማካይ በ0.8 በመቶ ብቻ አድጓል፤ ይህም በታዳጊ አገሮች ከተመዘገበው የ1.9 በመቶ ዕድገት አንጻር ዝቅተኛ ነው።

ወጣቶቻችን ዕድሉ ከተሰጣቸው ንድፍ የማውጣትና ማሽኖችን የመፍጠር አቅም አላቸው። የአፍሪካ ወጣቶች ይህ ብቃት ስላላቸው። ነገር ግን በቅድሚያ ያላቸውን ክህሎት፣ ዕውቀትና ጥበብ ማውጣት እንዲችሉ መንገዶችን መክፈት ይኖርብናል። በአግባቡ ካደራጀናቸው ደግሞ የተደበቀ ችሎታቸውን ይፋ ያደርጋሉ” ሲሉ

ቤጃይ ናይከር ነራሽ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

አፍሪካ ለእርሻና ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ ማሽኖችን በራሷ ለማምረት ምን ይጎድላታል? መሐንዲሶቿ የቴክኖሎጂ ሸማች ሳይሆኑ ፈጣሪ ቢሆኑስ? በዛሬው የ"ድራም ኦቭ ቼንጅስ" ዝግጅታችን ይህንን ለውጥ ከሚመሩ አፍሪካውያን መካከል አንዱን እንግዳ አድርገናል። እንግዳችን ኢትዮጵያዊው ሥራ ፈጣሪና የኢንዱስትሪ መሐንዲስ እንዲሁም የቤጃይ ኢትዮ ኢንዱስትሪያል ኤንድ ኢንጂነሪንግ ሶሉሽንስ መሥራች ቤጃይ ናይከር ነራሽ ናቸው።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0