የኮንትሮባንድ ንግድ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች የወጪ ንግድን እየጎዳ መሆኑን የዘርፉ ላኪዎች ማኅበር አስጠነቀቀ
18:32 25.11.2026 (የተሻሻለ: 18:34 25.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኮንትሮባንድ ንግድ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች የወጪ ንግድን እየጎዳ መሆኑን የዘርፉ ላኪዎች ማኅበር አስጠነቀቀ
ድንበር ተሻጋሪ የኮንትሮባንድ ንግድ የኢትዮጵያን መደበኛ የጥራጥሬና የቅባት እህሎች የወጪ ንግድ ክፉኛ እየጎዳው መሆኑን የኢትዮጵያ ጥራጥሬ፣ ቅባት እህሎችና ቅመማ ቅመም ላኪዎች ማኅበር አስታውቋል።
መንግሥት ሕገ-ወጥ ንግድን ለመግታት ጥረት ቢያደርግም ምርቶች አሁንም በኮንትሮባንድ ከሀገር እየወጡ በመሆኑ ጠንካራ የሕግ ማስከበር እርምጃ ያስፈልጋል መባሉን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ምቹ የአየር ንብረት ቢኖራትም ከዘርፉ አቅሟ እየተጠቀመች ያለችው 30% ብቻ ሲሆን እስከ 25% የሚደርስ የድህረ-ምርት ብክነትም ሌላው ፈተና መሆኑ በ15ኛ ዓለም አቀፍ የጥራጥሬና ቅባት እህሎች ጉባኤ ላይ ተጠቁሟል።
ሀገሪቱ ባለፈው ዓመት 555 ሺህ ሜትሪክ ቶን የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ምርት ወደ ውጭ በመላክ ከ571 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ ተመላክቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X