አዲሱ የሩሲያ ፀረ-ድሮን ሥርዓት የጠላት ድሮኖችን የቀጥታ ምስል ማስተላለፍና ዒላማዎችን መከታተል ይችላል – የኩባንያው ተወካይ
17:55 25.11.2026 (የተሻሻለ: 18:04 25.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
አዲሱ የሩሲያ ፀረ-ድሮን ሥርዓት የጠላት ድሮኖችን የቀጥታ ምስል ማስተላለፍና ዒላማዎችን መከታተል ይችላል – የኩባንያው ተወካይ
አዲስ ይፋ የሆነው ካሽቼይ የተሰኘው የድሮን መለያ መሣሪያ በሩሲያ ተወዳዳሪ የሌለው መሆኑን የድሮን ዲፌንስ ኩባንያ ተወካይ ኢልዳር አልማዞቭ በሞስኮ ከተካሄደው የኢንተርፖሊቴክስ አውደ ርዕይ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
የድሮን መለያ መሣሪያው ልዩ ባኅሪያት፦
የድሮን ምልክቶችን መለየት ብቻ ሳይሆን ድሮኑ የሚሠራበትን ፍሪኩዌንሲ ማሳየት፣
በተጨማሪም ከኤፍፒቪ ድሮኖች የሚተላለፉ የቀጥታ ቪዲዮ ምስሎችን መጥለፍና ማሳየት።
ይህ መለያ መሣሪያ በሰዓት እስከ 330 ኪሎ ሜትር መምዘግዘግ ከሚችልና ዒላማዎችን በራሱ መከታተል ከሚችል ካሽቼይ ጠላፊ ድሮን ጋር በጥምረት የሚሠራ መሆኑንም አክለዋል።
ተወካዩ ሩሲያ በፀረ-ድሮን ቴክኖሎጂ ልማት ያካበተችውን ልምድ፤ በተግባር ሳይሆን በንድፈ ሐሳብ ላይ ከተመሠረቱ የሌሎች ሀገራት አምራቾች ሲነጻጸር ወሳኝ ብልጫ እንደሚሰጣትም ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X