የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴኔጋልን የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት ያጸናውን የፍርድ ቤት ውሳኔ ይግባኝ ሊል ነው

© telegram sputnik_ethiopiaየሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴኔጋልን የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት ያጸናውን የፍርድ ቤት ውሳኔ ይግባኝ ሊል ነው
የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴኔጋልን የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት ያጸናውን የፍርድ ቤት ውሳኔ ይግባኝ ሊል ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.11.2026
ሰብስክራይብ

የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሴኔጋልን የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊነት ያጸናውን የፍርድ ቤት ውሳኔ ይግባኝ ሊል ነው

የሞሮኮ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት (ካስ) ኅዳር 15 ቀን በ2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሴኔጋል 1 ለ 0 ያሸነፈችበትን ውጤት ያጸናበትን ውሳኔ ተቃውሟል።

ዋና ዋና ዝርዝሮች፦

▪ ፌዴሬሽኑ የግልግል ዳኝነቱን ታማኝነት አደጋ ላይ በጣሉ ድርጊቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ያቀረበውን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ ከግምት ውስጥ ባለማስገባቱ 'መገረሙንና ተቃውሞውን' ገልጿል። ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን ይግባኝ ለማለት ያሉትን ሁሉንም ሕጋዊ መንገዶች ለመጠቀም መወሰኑን አረጋግጧል።

▪ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤቱ ውሳኔ፤ ተጫዋቾች ያለ ዳኛ ፈቃድ ሜዳውን ለቅቀው እንዳይወጡ የሚከለክለውንና በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር ቦርድ እና በፊፋ በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገውን አሠራር ከግምት ውስጥ አላስገባም ሲል ፌዴሬሽኑ ተከራክሯል።

▪ የካስ ፍርድ፤ የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ካፍ ቀደም ሲል የሰጠው ውሳኔ እንዲሻር ያቀረበውን ይግባኝ ተከትሎ የመጣ ነው።

ℹ 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከታኅሣሥ 21 ቀን 2025 እስከ ጥር 18 ቀን 2026 በሞሮኮ አስተናጋጅነት ተካሂዷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0