አንጋፋው የኖሊዉድ ተዋናይ ፒት ኢዶቺ በፕሮስቴት ካንሰር ሕመም በ79 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

© telegram sputnik_ethiopiaአንጋፋው የኖሊዉድ ተዋናይ ፒት ኢዶቺ በፕሮስቴት ካንሰር ሕመም በ79 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አንጋፋው የኖሊዉድ ተዋናይ ፒት ኢዶቺ በፕሮስቴት ካንሰር ሕመም በ79 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.11.2026
ሰብስክራይብ

አንጋፋው የኖሊዉድ ተዋናይ ፒት ኢዶቺ በፕሮስቴት ካንሰር ሕመም በ79 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ስፑትኒክ አፍሪካ በአኅጉሪቱ የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ውስጥ ታሪካዊ አሻራ እንዲያኖሩ ያስቻሏቸውን ወሳኝ ክስተቶችና እውነታዎች ይዳስሳል፦

ለዝና ያበቃቸው ገጸ ባሕሪ፦ ፔት ኤዶቺ በትወና ዓለም ላይ ሳሉ በ1980ዎቹ በናይጄሪያ ቴሌቪዥን ባለሥልጣን በተዘጋጀው የቺኑዋ አቼቤ Things Fall Apart የቴሌቪዥን ድራማ ላይ የኦኮንኮውን ገጸ ባሕሪ በመላበስ ባቀረቡት የማይረሳ ትወና በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አትርፈዋል።

ከሬዲዮ ወደ ቴሌቪዥን፦ የሲኒማ ኮከብ ከመሆናቸው በፊት በጋዜጠኝነት ሙያ ስኬታማ ነበሩ። በ1967 በጀማሪ ፕሮግራም ረዳትነት አንድ ያሉት ኤዶቺ፤ በፈጣን የእርከን ዕድገት ወደ ዳይሬክተርነት፤ ከዚያም ወደ ሙሉ ጊዜ ትወና ተሸጋግረዋል።

ታላቁ አባወራ፦ ከኖሊዉድ ታላላቅ ተዋንያን አንዱ የሆኑት ኤዶቺ፤ በቀልብ ሳቢ ትወናቸው ይታወቃሉ። በተለይም ባሕላዊ የቤተሰብ አለቃና የአባትነት ሚናዎችን በተደጋጋሚ ተጫውተዋል።

ብሔራዊ ክብርና ሽልማቶች፦ ለፊልም ኢንዱስትሪው ላበረከቱት ታላቅ አስተዋፅዖ የናይጀር ብሔራዊ ኒሻንን እንዲሁም ከአፍሪካ ፊልም አካዳሚ የሕይወት ዘመን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ቺፍ ኤዶቺ ባለቤታቸው ባሪስተር ጆሴፊን ኤዶቺንና ስድስት ልጆቻቸውን ትተው አልፈዋል።

ፔት ኤዶቺ በ Things Fall Apart የቴሌቪዥን ድራማ ላይ ኦኮንኮውን ሆነው የተወኑበትን ቪዲዮ ይመልከቱ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0