ዩክሬን በቤንጋዚ ወደብ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሁለት የሊቢያ ወታደራዊ አባላት መገደላቸው ተሠማ
15:33 25.11.2026 (የተሻሻለ: 15:34 25.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ዩክሬን በቤንጋዚ ወደብ ላይ በፈጸመችው ጥቃት ሁለት የሊቢያ ወታደራዊ አባላት መገደላቸው ተሠማ
ግለሰቦቹ ኅዳር 13 ቀን በተፈጸመው ጥቃት በደረሰባቸው ጉዳት ሕይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍለ ጦር ዕዝ አስታውቋል።
▪ጥቃቱ በቤንጋዚ ወደብ የሚገኙ የሩሲያ መርከቦችን ዒላማ ያደረገ ነበር።
▪ የሊቢያ ፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት ድርጊቱን የብሔራዊ ሉዓላዊነት ጥሰት ነው ሲል አውግዞታል።
▪ የሊቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ከዩክሬን ይፋዊ ማብራሪያ የጠየቀ ሲሆን የሊቢያ ግዛትና ውኃዎች ለውጭ ግጭቶች መድረክ ሆነው ማገልገል እንደሌለባቸው አሳስቧል።
የዩክሬን ድሮን በቤንጋዚ የባሕር ዳርቻ አቅራቢያ በሚገኝ መርከብ ላይ ጥቃት ሲፈጽም ያሳያል የተባለ ከማኅበራዊ ትስስር ገጾች የተገኘ ተንቀሳቃሽ ምሥል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X