ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች

 

ይህ የተገለጸው በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ትብብር ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ በአዲስ አበባ በተካሄደው 5ኛው የአፍሪካ ቀንድ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አምባሳደር አዳም ተስፋዬ፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ እና አኅጉራዊ ውህደት ቁርጠኛ እንደሆነች እና በውይይት፣ በዲፕሎማሲ፣ በዓለም አቀፍ ሕግ እና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ አስተማማኝ እና ዘላቂ የባሕር በር ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል በመድረኩ ላይ መድረክ ገልጸዋል።

 

“የቀይ ባሕር ደኅንነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት የማይነጠል አካል እንደሆነ በጽኑ እናምናለን” ማለታቸውንም የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0