ሁለት የሱዳን ኃይሎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የድርድር ሃሳብ እንደሚቀበሉ ገለፁ

ሁለት የሱዳን ኃይሎች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የድርድር ሃሳብ እንደሚቀበሉ ገለፁ
የሱዳን የአብዮታዊ ኃይሎች ሲቪል ዴሞክራሲያዊ ጥምረት (ሶሙድ) እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የሚደገፈው የሽግግር የሰላም መንግሥት፤ የኢትዮጵያ መሪ በሱዳን ያለውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ሁሉንም ወገኖች ያሳተፈ ውይይት በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ያቀረቡትን ጥሪ በደስታ መቀበላቸውን የሀገሪቱ ሚዲያ አስነብቧል።
የሲቪል ጥምረቱ ምላሽ፦
ጥምረቱ ባወጣው መግለጫ፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥሪ በኢትዮጵያና በሱዳን ሕዝቦች መካከል ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር እንዲሁም አዲስ አበባ ለሱዳን አንድነት፣ የግዛት አንድነትና መረጋጋት ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብሏል።
ኢትዮጵያ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አል-በሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ለሱዳን ዴሞክራሲያዊ ሽግግር የነበራትን ወሳኝ የሽምግልና ሚናም አድንቋል።
የሽግግር የሰላም መንግሥቱ አቋም፦
◻ የአስተዳደሩ የማስታወቂያ ሚኒስትር እና ቃል አቀባይ ካሊድ አህመድ ዳና እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ከሱዳን ሕዝብ ጎን በመቆሟና ለሀገሪቱ ሉዓላዊነት እና አንድነት ላሳያቸው ቁርጠኝነት ምሥጋና አቅርበዋል።
◻ ጦርነቱን ለማስቆም እና የግጭቱን መንስኤዎች ከሥሩ ለመፍታት በሚደረገው ውይይት ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X