ሩሲያ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ የምዕራባውያንን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበላይነት ተቃወመች

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ የምዕራባውያንን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበላይነት ተቃወመች
ሩሲያ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ የምዕራባውያንን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበላይነት ተቃወመች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.11.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ የምዕራባውያንን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበላይነት ተቃወመች

ምዕራባውያን ሀገራት ተቃውሞ ቢያነሱም የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ሁለተኛ ኮሚቴ፤ ሩሲያ ያቀረበችውን የሰው ሠራሽ አስተውህሎት የውሳኔ ሐሳብ ማጽደቁን፤ በተመድ የሩሲያ ምክትል ቋሚ መልዕክተኛ ዲሚትሪ ቹማኮቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ሰው ሠራሽ አስተውህሎት ለጋራ ጥቅም መዋል ያለበት ቴክኖሎጂ መሆኑን የገለጹት ዲፕሎማቱ፤ "በጥቂት ሀገራትና ኮርፖሬሽኖች ሳይታዘዙ የራሳቸውን የዲጂታል መጻዒ ዕድል መገንባት የሚፈልጉ ሀገራት ለተነሳሽነቱ ድጋፍ ሰጥተዋል” ሲሉ ከድምፅ አሰጣጡ በኋላ ተናግረዋል።

የውሳኔ ሐሳቡ፦

ሰው ሠራሽ አስተውህሎት በጥቂት ሀገራትና ኮርፖሬሽኖች ብቻ በብቸኝነት መያዙን ይቃወማል፣

በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የሰው ሠራሽ አስተውህሎት ቴክኖሎጂዎችን በስፋት እንዲያገኙ ጥሪ ያቀርባል፣

ወታደራዊ አጠቃቀሞች ከውሳኔው ማዕቀፍ ውጭ መሆናቸውን በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

ተነሳሽነቱ በ79 የድጋፍ፣ በ57 የተቃውሞ እና በ42 የተአቅቦ ድምፅ ጸድቋል።

የውሳኔ ሐሳቡ ከፖለቲካዊ አንድምታዎች ነፃ ተደርጎ ቢረቀቅም፤ ምዕራባውያን ሀገራት የተለያዩ ሰበቦችን በመጠቀም በወሳኝ ጉዳዮች ላይ የሚተላለፉ ውሳኔዎችን ለማዘግየት ተቃውሞ ማንሳታቸውን ምክትል የተመድ መልዕክተኛው ተናግረዋል።

ይህ አቋማቸው በተለይ በቴክኖሎጂ መጋራትና በልማት ድጋፍ ዙሪያ በተደረጉ ውይይቶች ላይ በግልጽ መታየቱንም አክለዋል።

የሩሲያ የውሳኔ ሐሳብ በታኅሣሥ ወር በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ይቀርባል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0