- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የሼንዘን መግለጫ፡ ለተቀረው ዓለም ምን ትርጉም አለው?

የሼንዘን መግለጫ፡ ለተቀረው ዓለም ምን ትርጉም አለው?
ሰብስክራይብ
የቻይና፣ የሩሲያ እና የአሜሪካ መሪዎች በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሼንዘን ፊት ለፊት ተገናኝተው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማሻሻያ፣ በሃይል ደህንነት እና የኒውክሌር ስጋትን በመቀነስ ዙሪያ የጋራ መግለጫ አወጡ።

ለአፍሪካ ይህ [የሦስትዮሽ ጉባኤው] በበጎ የሚታይ መልካም አጋጣሚ ነው፤ ምክንያቱም የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በእኩል የአህጉራት ውክልና እና በሉዓላዊ እኩልነት መርህ ማዋቀር፣ እንዲሁም ሰባቱን ታላላቅ አህጉራት በፍትሃዊነት የሚወክል ጠንካራ የፀጥታው ምክር ቤት መፍጠርን የመሳሰሉ የአፍሪካ ጉዳዮች እንዲነሱ ያደርጋል” ሲሉ ዳዊት መዝገበ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

ሦስት ዓለም አቀፍ ኃያላን መንግሥታት ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኙ። ውይይታቸውም በኃይል፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ማሻሻያ እና በኒውክሌር ስጋት ዙሪያ ያተኮረ ነበር። ሆኖም የሼንዘን መግለጫ ለአፍሪካ እና ለተቀረው ዓለም ምን ትርጉም ሊኖረው ይችላል? የዛሬው "ድራም ኦቭ ቼንጅስ" ዝግጅታችን፣ ጸሐፊ እና ተመራማሪ እንዲሁም በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑትን ዳዊት መዝገበ (ዶ/ር) በመጋበዝ በእነዚህ ወሳኝ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደርጋል።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0