- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እና ምርምር ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚሰጠው ፋይዳ

የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እና ምርምር ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚሰጠው ፋይዳ
ሰብስክራይብ

ምርምርን በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ውስን ሀብት ባለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ለልማት 'የአቅም ማባዣ' (force multiplier) አድርጌ እገልጸዋለሁ። ሀብት ውስን በሚሆንበት ጊዜ ዋናው ፈተና የሀብቱ እጥረት ሳይሆን ያንን ያለውን ሀብት ምን ያህል በብቃትና በአግባቡ እየተጠቀምንበት ነው የሚለው ነው። ምርምር እጅግ ወሳኝ የሚሆነውም እዚህ ቦታ ላይ ነው - ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ፋከልቲ ከፍተኛ የምርምር ባለሙያ ሰለሞን አስማረ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራማችን በክፍል አንድ፦ ዓለም አቀፍ ፍትሕን በሰፊ እይታ ለመመልከት፣ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) ከአውሮፓዊ ማዕከላዊነት መሠረቶቹ ተላቆ ለምን መሻሻል እንዳለበት እንወያያለን።

መሐመድ አወል ሐጎስ፣ ማኅበራዊ አንትሮፖሎጂስትና በወራቤ ዩኒቨርሲቲ መምህር ደግሞ እንግዳችን ናቸው።

📈 በክፍል ሁለት፦ ከምርምር ወደ ዕድገት፦ በአፍሪካ የአካዳሚክ ተቋማትና የኢንዱስትሪ ዘርፍ መካከል ያለውን የትብብር ክፍተት ስለመሙላት ከሰለሞን አስማሬ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ፋኩልቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ጋር እንዳስሳለን።

🔊 በእንግሊዘኛ የቀረበው ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡ ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0