የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዋጋ ጭማሪ እና የክብደት ማጉደል ጥሰት በፈጸሙ 61 ዳቦ አምራቾች ላይ እርምጃ ወሰደ

© telegram sputnik_ethiopiaየአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዋጋ ጭማሪ እና የክብደት ማጉደል ጥሰት በፈጸሙ 61 ዳቦ አምራቾች ላይ እርምጃ ወሰደ
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዋጋ ጭማሪ እና የክብደት ማጉደል ጥሰት በፈጸሙ 61 ዳቦ አምራቾች ላይ እርምጃ ወሰደ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.11.2026
ሰብስክራይብ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዋጋ ጭማሪ እና የክብደት ማጉደል ጥሰት በፈጸሙ 61 ዳቦ አምራቾች ላይ እርምጃ ወሰደ

ቢሮው በመዲናዋ በሚገኙ 188 ዳቦ ቤቶች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ምልከታና ክትትል፤ የንግድ ሕጉን ተላልፈው በተገኙ 61 የዳቦ አምራቾች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

እርምጃ የተወሰደባቸው አምራቾች 70 ግራም ዳቦ ከ13 ብር በላይ ሲሸጡ፣ ከ70 ግራም በታች የሆነ ዳቦ ለገበያ ሲያቀርቡ እና የዋጋ ዝርዝር ሳይለጥፉ ሲሠሩ ተገኝተዋል።

ሸማቹ ማኅበረሰብ መሰል ሕገ-ወጥ የግብይት ተግባራት ሲያጋጥሙት ጥቆማ እንዲሰጥ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0