ከፍተኛ የዕዳ ጫና የአፍሪካን የወረርሽኝ ዝግጁነት እያዳከመ መሆኑን የኤይድስ ኬር ፋውንዴሽን አስጠነቀቀ

© telegram sputnik_ethiopiaከፍተኛ የዕዳ ጫና የአፍሪካን የወረርሽኝ ዝግጁነት እያዳከመ መሆኑን የኤይድስ ኬር ፋውንዴሽን አስጠነቀቀ
ከፍተኛ የዕዳ ጫና የአፍሪካን የወረርሽኝ ዝግጁነት እያዳከመ መሆኑን የኤይድስ ኬር ፋውንዴሽን አስጠነቀቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.11.2026
ሰብስክራይብ

ከፍተኛ የዕዳ ጫና የአፍሪካን የወረርሽኝ ዝግጁነት እያዳከመ መሆኑን የኤይድስ ኬር ፋውንዴሽን አስጠነቀቀ

እየጨመረ የመጣው የውጭ ዕዳ ጫና የአፍሪካ ሀገራት ለጤና አገልግሎትና ለወረርሽኝ ዝግጁነት ሊያውሉ የሚገባቸውን ውስን ሀብት ለዕዳ ክፍያ እንዲመድቡ እያስገደዳቸው ነው ሲሉ የፋውንዴሽኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፔኒናህ ኢቱንግ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው 5ኛው የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጎን ለጎን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

“ሀገራት የውጭ ዕዳቸውን ከመክፈልና የሕዝባቸውን ጤና ከመጠበቅ አንዱን እንዲመርጡ መገደድ የለባቸውም፤ የዕዳ እፎይታና መልሶ ማዋቀር እንዲሁም የሀገር ውስጥ የሀብት ማሰባሰብ አቅምን ማጠናከር ያስፈልጋል” ማለታቸውን ጠቅሶ የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛ ዘግቧል።

በተጨማሪም አፍሪካ በዓለም አቀፍ የጤና ድርድሮች ያላትን የጋራ ድምፅ ማጠናከርና ለክትባቶች፣ ለመድኃኒቶችና ለሌሎች ወሳኝ የጤና ቴክኖሎጂዎች ፍትሐዊ ተደራሽነት መታገል እንዳለባትም ገልጸዋል።

ተቋማቸው ከጉባኤው ጎን ለጎን የውጭ ዕዳ በሕዝብ ጤና ፋይናንስ ላይ ያለውን ተጽዕኖና አፍሪካ የዓለም አቀፍ የጤና ሥርዓትን በመቅረጽ ረገድ ያላትን ተጽዕኖ ለማጠናከር ያለሙ ሁለት ውይይቶችን ስለማዘጋጀቱም ተናግረዋል።

አዳዲስ ዜናዎች
0