የዩክሬን ወታደራዊ ሎጂስቲክስ በሩሲያ ጥቃት በእጅጉ ተገቷል - ባለሙያ

ሰብስክራይብ

የዩክሬን ወታደራዊ ሎጂስቲክስ በሩሲያ ጥቃት በእጅጉ ተገቷል - ባለሙያ

በኪየቭ ድልድዮች ላይ እየተካሄዱ ያሉት ተከታታይ የሩሲያ ጥቃቶች፤ የዩክሬን ወታደራዊ የአቅርቦት መስመሮችን በከፍተኛ ሁኔታ እንደገቱ ሩሲያዊው የወታደራዊ ጉዳዮች ባለሙያ የቭጌኒ ሚካይሎቭ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ባለሙያው ያነሷቸው ሌሎች ዋና ዋና ነጥቦች፦

◻ ተገማች መስመሮች፦ የትራፊክ ፍሰቱን ወደ ቀሩት ድልድዮች ማዘዋወር መጨናነቅና መዘግየት ከመፍጠር ባለፈ፤ የአቅርቦት መስመሮችን ይበልጥ ለጥቃት ተጋላጭ ያደርጋቸዋል።

◻ የደቡባዊ ድልድይ መመታት፦ በዚህ ወሳኝ የመኪና እና የባቡር መሻገሪያ ላይ የደረሰው ጉዳት፤ የድኔፐር ወንዝ መሻገሪያ ላይ ስጋት ደቅኗል።

◻ የወንዙ የግራ ዳርቻ ለአደጋ ተጋልጧል፦ ያለ ባቡር ትስስር በግራ ዳርቻ የሚገኙ የዩክሬን ኃይሎች ከባድ የጦር መሣሪያዎችና ነዳጅ ለማጓጓዝ በመንገድ ትራንስፖርት ላይ ለመወሰን ይገደዳሉ፤ ይህ ደግሞ አዝጋሚ፣ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ እና ለከፋ ጥቃት ተጋላጭ ነው።

ይህንን የባቡር አቅም ማጣት ከጊዜያዊ መጓተት ባለፈ፤ የሎጂስቲክስ ሰንሰለቱ ሙሉ በሙሉ እንዲበጠስ ሊያደርግ ይችላል ሲሉ ሚካይሎቭ አጠቃለዋል።

በኪየቭ ለዩክሬን ጦር የሎጂስቲክስ አገልግሎት የሚሰጥ ድልድይ ሲመታ የሚያሳይ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ተንቀሳቃሽ ምሥል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0