የአውሮፓ ኅብረት እና የሩዋንዳ የስደተኞች ስምምነት በምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን በገንዘብ የመደገፍ ስጋት አለው - የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopiaየአውሮፓ ኅብረት እና የሩዋንዳ የስደተኞች ስምምነት በምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን በገንዘብ የመደገፍ ስጋት አለው - የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
የአውሮፓ ኅብረት እና የሩዋንዳ የስደተኞች ስምምነት በምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን በገንዘብ የመደገፍ ስጋት አለው - የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.11.2026
ሰብስክራይብ

የአውሮፓ ኅብረት እና የሩዋንዳ የስደተኞች ስምምነት በምሥራቃዊ ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን በገንዘብ የመደገፍ ስጋት አለው - የኮንጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

"ያለመረጋጋት፣ የግጭት እንዲሁም የመፈናቀል እና የግዳጅ ስደት እምብርት የሆነች ሀገር፤ መጠለያ እና […] ዓለም አቀፍ ሕግን የምታከብር ታማኝ አጋር ተደርጋ መታየቷ ግራ የሚያጋባ ነው" ሲሉ ቴሬዝ ካይክዋምባ ዋግነር ለአንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ዋና ዋና ስጋቶችንም እንደሚከተለው ዘርዝረዋል፦

▪ግጭትን በገንዘብ መደገፍ፦ የአውሮፓ ኅብረት የሚሰጠው ገንዘብ በአሜሪካ ማዕቀቦች ምክንያት የተፈተነውን የሩዋንዳን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመሸፈን፤ አማጽያንን ለመደገፍ ሊውል ይችላል የሚል ስጋት በኪንሻሳ በኩል አለ።

▪ስትራቴጂካዊ ማዘናጊያ፦ ስምምነቱ ኪጋሊ የታላላቅ ሐይቆች ቀጣናን በማተራመስ ረገድ ያላትን ሚና የመሸፈን አደጋ አለው።

ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፤ ሩዋንዳ በምሥራቃዊ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱትን የኤም23 አማጽያንን ትደግፋለች ስትል በተደጋጋሚ የምትከስ ቢሆንም፤ ኪጋሊ ግን ክሱን ታስተባብላለች።

ኦስትሪያ፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ዴንማርክ እና ኔዘርላንድስ ከሩዋንዳ ጋር በመሆን፤ ከአውሮፓ ኅብረት ውጭ የስደተኞች መመለሻ ማዕከል ማቋቋም የሚችሉበትን መንገድ እያጤኑ እንደሆነ ቀደም ሲል ተዘግቧል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0