የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ለኮፕ 32 ዝግጅት ያላትን ጽኑ ድጋፍ በድጋሚ አረጋገጠች

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እና ለኮፕ 32 ዝግጅት ያላትን ጽኑ ድጋፍ በድጋሚ አረጋገጠች
ይህ የተገለፀው የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታዎች ሁለተኛውን ዙር የጋራ የፖለቲካ ምክክር መድረክ በአዲስ አበባ ባካሄዱበት ወቅት ነው።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን ምን አሉ?
🟠 ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና ከዚያም ባሻገር ለምትጫወተው ስትራቴጂካዊ ሚና ዕውቅና ሰጥተዋል፣
🟠 ሀገራቸው ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ አንድነት እና የግዛት ሙሉዕነት ያላትን ሙሉ ድጋፍ አረጋግጠዋል፣
🟠 ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው የኮፕ 32 ጉባኤ ስኬት ሀገራቸው ድጋፏን እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ያነሷቸው ነጥቦች፦
የኤምሬቶች ባለሀብቶች በቴሌኮም፣ በባንክ፣ በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን፣ በኢነርጂ፣ በሎጂስቲክስ፣ በቱሪዝም እና በአይሲቲ ዘርፎች ኢንቨስትመንታቸውን እንዲያሰፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ለኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ምርቶች የገበያ ዕድል እንዲሰፋ ጠይቀዋል።
የጋራ የፖለቲካ ምክክሮችን ማጠናከር፣ በየጊዜው ከፍተኛ ደረጃ የልዑካን ልውውጦችን ማካሄድ እንዲሁም አሁን ያሉትን የሁለትዮሽ ስምምነቶች መገምገምና በተግባር ላይ ማዋል እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X