ወደ 1,000 የሚጠጉ የፈረንሳይ ወታደራዊ ባለሙያዎች በዩክሬን ይገኛሉ - ሩሲያዊ ባለሙያ
11:28 24.11.2026 (የተሻሻለ: 11:34 24.11.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ወደ 1,000 የሚጠጉ የፈረንሳይ ወታደራዊ ባለሙያዎች በዩክሬን ይገኛሉ - ሩሲያዊ ባለሙያ
"እነዚህም የግል ወታደራዊ ኩባንያዎች አባላት እንዲሁም የጦር መሣሪያ አቅርቦት፣ ሥልጠና እና ስትራቴጂካዊ ወታደራዊ ጉዳዮችን የሚመሩ የፈረንሳይ ጄኔራሎችን ያካትታሉ" ሲሉ የሩሲያ የሮኬትና መድፈኛ ሳይንስ አካዳሚ አማካሪ ኦሌግ ኢቫኒኮቭ ለአንድ የሩሲያ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
ቅጥረኛ ፈረንሳውያን ወታደሮች ላለፉት በርካታ ዓመታት በሩሲያ ጥቃቶች ሲገደሉ መቆየታቸውንም ገልጸዋል።
ፈረንሳውያንን ጨምሮ የውጭ አሠልጣኞች የሚሠሩባቸው የዩክሬን ወታደራዊ ማሠልጠኛ ማዕከላት የሩሲያ ጦር ቀዳሚ ዒላማዎች እንደሆኑ የሩሲያ ጀግና ሜጀር ጄኔራል ሰርጌይ ሊፖቮይ ቀደም ሲል መግለጻቸው ይታወሳል።
ኅዳር 8 ቀን ፓሪስ ወታደራዊ ባለሙያዎቿ በዩክሬን ምድር እንደሚገኙ ማረጋገጧ ይታወቃል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X