የ2027ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የሚያስተናግዱ ስድስት ከተሞች ይፋ ሆኑ
09:33 24.11.2026 (የተሻሻለ: 09:34 24.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የ2027ቱን የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የሚያስተናግዱ ስድስት ከተሞች ይፋ ሆኑ
የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በናይጄሪያ አቡጃ ያካሄደውን 48ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተከትሎ የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር የሚካሄድባቸውን ቦታዎች በይፋ አጽድቋል።
ውድድሩን የሚያስተናግዱት ስድስቱ ከተሞች፦
ናይሮቢ (ኬንያ)
ዳሬሰላም፣ አሩሻ እና ዛንዚባር (ታንዛኒያ)
ካምፓላ እና ሆይማ (ኡጋንዳ)
ናይሮቢ 60 ሺህ ተመልካቾችን የሚይዘውንና በጥር 2027 ይመረቃል ተብሎ የሚጠበቀውን አዲሱን ታላንታ ስታዲየም ለውድድሩ ትጠቀማለች።
ኡጋንዳ በበኩሏ ካምፓላ በሚገኘው ማንዴላ ብሔራዊ ስታዲየም እና አዲስ በተገነባው ሆይማ ሲቲ ስታዲየም ጨዋታዎችን ታስተናግዳለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X