- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የራሽያ-አፍሪካ የኃይል ትብብር እና የኃይል ሉዓላዊነት

የራሽያ-አፍሪካ የኃይል ትብብር እና የኃይል ሉዓላዊነት
ሰብስክራይብ

እያንዳንዷ ሀገር የራሷን የኃይል ሽግግር የማስተዳደር ሉዓላዊ መብቷን እንድታስጠብቅ ያስችላታል። ስለዚህ ማንም መጥቶ ይህንን ለእኛ ማስተዳደር አይኖርበትም። ኃላፊነቱን በባለቤትነት እንይዛለን፤ ቁጥጥሩም በእጃችን ይቆያል። ብድራችንን በአግባቡ እንከፍላለን፤ ምን ለማድረግ እንደተስማማን እና እነዚህን ብድሮች እንዴት እንደምንከፍልም በግልጽ እናውቃለን። በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ጉዳዩን በራሳችን አቅም ማከናወን እንችላለን፤ የሉዓላዊ መብቶቻችንም መጠበቃቸውን እናረጋግጣለን። ይህ ደግሞ እጅግ መሠረታዊ ነገር ይመስለኛል። በአፍሪካ ዘላቂ የኃይል መፍትሔን ለማፈላለግ በምንጥርበት በዚህ ወቅት፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከተማርናቸው ትምህርቶች በመነሳት አንድ ነገር መወሰድ ካለበት፣ ወደፊት በፍጹም መጠበቅ ያለበት ዋነኛ ነገር ይህንን ነው።” — ፌይዝ ምካችዋ፣ በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ የኃይል ልማት ኢንስቲትዩት የኃይል ቆጣቢነት እና የፍላጎት አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ

በዛሬው የ"ኮንቲነንታል ድሪፍት" ዝግጅታችን፣ የራሽያ-አፍሪካ የኃይል ትብብርን፣ የጋዝ መሠረተ ልማትን፣ የኃይል ደህንነትን እና የአፍሪካን የኢንዱስትሪ ልማት አቅጣጫዎች እንፈትሻለን። ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ የኃይል ልማት ኢንስቲትዩት የኃይል ቆጣቢነት እና የፍላጎት አስተዳደር ዋና ሥራ አስኪያጅ ከሆኑት ከፌይዝ ምካችዋ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0