ታጂኪስታን ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

© telegram sputnik_ethiopiaታጂኪስታን ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች
ታጂኪስታን ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.11.2026
ሰብስክራይብ

ታጂኪስታን ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ለመውጣት ይፋዊ ጥያቄ አቀረበች

​ሀገሪቱ የዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) መመሥረቻ ስምምነት ከሆነው የሮም ስምምነት መውጣቷን ዓርብ ለተመድ በይፋ አሳውቃለች። በስምምነቱ ድንጋጌዎች መሠረትም ውሳኔው ከአንድ ዓመት በኋላ ማለትም ኅዳር 10 ቀን 2020 ዓ.ም በይፋ ተግባራዊ ይሆናል።

​አይሲሲ በዓለም አቀፍ መድረክ ተደጋጋሚ ትችቶችን ሲያስተናግድ ቆይቷል። ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንደገለጹት፤ በሩሲያ-ቻይና-አሜሪካ ጉባኤ ወቅት መሪዎቹ የፍርድ ቤቱ ወሳኔዎች ፖለቲካዊ አጀንዳ እንዳላቸው አንስተው መግባባት ላይ ደርሰዋል።

​ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በበኩላቸው፤ ተቋሙ የምዕራባውያን ጥምረት “ትዕዛዝ ፈጻሚ” እና የፖለቲካ ጫና ማሳደሪያ መሣሪያ ነው ሲሉ ከሰዋል።

​ይህ ውሳኔ መቀመጫውን ሄግ ባደረገው ፍርድ ቤት ላይ በተለይም በአፍሪካ አኀጉር መጠነ ሰፊ ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ የመጣ ነው።

​🟠 ብሩንዲ እ.ኤ.አ በጥቅምት 2017 ከዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በይፋ በመውጣት የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

​🟠 እ.ኤ.አ በ2026 ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒጀር ፍርድ ቤቱን “አድሏዊ” እና “አዲስ ቅኝ ግዛታዊ” ፍትሕ የሚያራምድ ነው በማለት፤ ከስምምነቱ ለመውጣት ይፋዊ ደብዳቤ ለተመድ አስገብተዋል። ቻድም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዳለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0