ጋና የ2026 የዓለም የአካል ጉዳተኞች እግር ኳስ ዋንጫን አሸነፈች

ሰብስክራይብ

ጋና የ2026 የዓለም የአካል ጉዳተኞች እግር ኳስ ዋንጫን አሸነፈች

የጋናው ብላክ ቻሌንጅ ቡድን በሜክሲኮ ሳን ሁዋን ዴ ሎስ ላጎስ በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፤ ሞሮኮን 1 ለ 0 በማሸነፍ ዋንጫውን ለመጀመሪያ ጊዜ ማንሳቱን የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

የቡድኑ አምበል ሪቻርድ ኦፔንቲል በ32ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ግብ አስቆጥሯል።

የፍጻሜ ጨዋታው የ2024 የአፍሪካ የአካል ጉዳተኞች እግር ኳስ ዋንጫ እና የ2023 የአፍሪካ የአካል ጉዳተኞች ጨዋታ ተፋላሚዎችን ያገናኘ ሲሆን በሁለቱም ውድድሮች ጋና አሸናፊ ነበረች።

ጋና፤ አንጎላ በ2018 ውድድሩን ካሸነፈች በኋላ ዋንጫውን ያነሳች ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ሆናለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0